የአየር ንብረት ለውጥ ድንጋጌ ቀናት ከፈጁ ክርክሮች ከተካሔደበትና የማሻሻያ ምክረ ሃሳቦች ከታከለበት በኋላ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤትን ይሁንታ አገኘ።
የይሁንታ ድንጋጌው 37 ለ30 በሆነ ድምፅ በ2030 ለ43 ፐርሰንት የአየር ብክለት ቅነሳ በማግኘት አልፏል።
የፌዴራል መንግሥቱ ድንጋጌው በሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ይሁንታን አግኝቶ ለማለፍ የበቃው የግሪንስ፣ ሴናተር ፖኮክና ሴናተር ጃኪ ላምቢን ድምፆች በታካይነት በማግኘት ነው።
የድንጋጌውን ማለፍ አስመልክቶም የፓስፊክ ደሴት አገራት በመልካም ጎኑ ተቀብለውታል። ይሁንና በማኅበረሰቦቻቸው ላይ ብርቱ አደጋን ለመከላከል ከዚህ የጠነከረ እርምጃ እንደሚያሻ አሳሰበዋል።
የማሻሻያ ምክረ ሃሳብ የታከለበት ድንጋጌ ለመጨረሻ የይሁንታ ድምፅ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመልሷል።
የቀብር ሥነ ሥርዓት
የወቅቱን ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚን ጨምሮ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ጆን ሐዋርድ፣ ቶኒ አበትና ማልከም ተርንቡል በዚህ ወር መጨረሻ ላይ በሚካሔደው የቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ የቀብር ሥነ ሥር ዓት ላይ ለመገኘት ወደ ጃፓን ያቀናሉ።
የቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር በወርኅ ጁላይ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የምርጫ ዘመቻ ቅስቀሳ እያካሔዱ ሳለ በአንድ ግለሰብ በተተኮሱ የበት ውስጥ ሠራሽ ጥይቶች ግድያ ተፈፅሞባቸው ነው።

Former Japanese Prime Minister Shinzo Abe at Joint Base Pearl Harbor Hickam's Kilo Pier on December 27, 2016 in Honolulu, Hawaii. Credit: Kent Nishimura/Getty Images
ጠቅላይ ሚኒስትር አልባኒዚ ሟቹ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር በጃፓንና አውስትራሊያን ኝኙነት ከፍ ለማድረግ ሁነኛ አስተዋፅዖ ማድረጋቸውን ለፓርላማ ተናግረዋል።
የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ሴፕቴምበር 27 ይፈፀማል።