ተዋናይ ዊል ስሚዝ ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት በኦስካር የሽልማት ሥነ ሥርዓቶች ላይ እንዳይገኝ ታገደ

***የተቃዋሚ ቡድን መሪ አንቶኒ አልባኒዚ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምርጫ ጥሪውን የማዘግየቱን ሁነት ልክ የጨዋታ ያህል እየቆጠሩት ነው ሲሉ ተቹ።

News

Will Smith. Source: Getty

ተዋናይ ዊል ስሚዝ በ94ኛው የኦስካር ሽልማት ሥነ ሥርዓት ወቅት የመድረክ አጋፋሪ የነበረውን ክሪስ ሮክ በጥፊ መማታቱን ተከትሎ ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት በኦስካር የሽልማት ሥነ ሥርዓቶች ላይ እንዳይገኝ ታገደ። 

እንዲሁም ለሚቀጥለው አንድ አሠርት ዓመት የተንቀሳቃሽ ምስል ሥነ ጥበብና ሳይንስ አክዳሚ ኩነቶች ላይ እንዳይገኝም ገደብ ተጥሎበታል። 

ይሁንና ቦርዱ ዊልል ስሚዝ ባለፈው ወር በ King Richard ትወናው ያገኘውን ምርጥ ተዋናይ የኦስካር ሽልማት እንዲነጠቅና ከወደፊት የኦስካር ሽልማት ዕጩነት ወይም አሸናፊነት እንዲታገድ ግና አልወሰነም። 

አገር አቀፍ ምርጫ

የተቃዋሚ ቡድን መሪ አንቶኒ አልባኒዚ ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን የፌዴራል ምርጫ ቀንን እስካሁን ባለመቁረጣቸው ትችት ሰነዘሩ።

የአገር አቀፍ ምርጫውን ለሜይ 14 ወይም ለሜይ 21 ለመጥራት ሁለት ቅዳሜዎች ብቻ ቀርተዋል። 

በነገው ዕለት እሑድ የምርጫ ቀን ቆረጣ ካልተደረገ የምክር ቤት አባላት በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ካንብራ ለመመለስ ግድ ይሰኛሉ።

አቶ አልባኒዚ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምርጫ ጥሪውን የማዘግየቱን ሁነት ልክ የጨዋታ ያህል እየቆጠሩት ነው፤ ምርጫው ሲጠራም ጠረጴዛ ላይ የሚያኖሯቸው ፖሊሲዎች እንደሌላቸውም ተናግረዋል። 

ዊል ስሚዝ

 


1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now