ሜልበርን ላይ የተጣለው የኮሮናቫይረስ ገደብ ነገ እኩለ ለሊት ላይ ይነሳል

*** ከዓርብ ጁን 11 ጀምሮ ትምህር ቤቶች ተማሪዎቻቸውን በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ማስተማር ይጀምራሉ።

SBS Amharic

Source: SBS Amharic

የቪክቶሪያ ተጠባባቂ ፕሪሚየር ጄምስ ሜሊኖ ሜልበርንና ሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ ተጥለው የነበሩት የኮሮናቫይረስ ገደቦች ከነገ ሐሙስ ጁን 10 ከምሽቱ 11.59pm ጀምሮ እንደሚነሳ ዛሬ አስታውቀዋል። 

በዚህም መሠረት፤

  • ማኅበራዊ

    ከዚህ ቀደም ከቤትዎ ለመውጣት ምክንያት የነበሩ አምስት ጉዳዮች ተነስተዋል።
    • መሠረታዊ ለሆኑ የገበያ ሸመታ
    • ለሌሎች ክብካቤ ለማድረግ
    • ፈቃድ ያለው የሥራ ገበታ ላይ ለመሠማራት
    • እስከ ሁለት ሰዓት የሚደርስ የአካል እንቅስቃሴ ለማድረግና
    • ክትባት ለመከተብና ልዩ ፈቃድ 
     የኪሎ ሜትሮች ገደብቀደም ሲል ከመኖሪያ ቤትዎ ርቀው መሔድ የሚችሉ እስከ 10 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ድረስ ብቻ የነበረው ከሐሙስ እኩለ ለሊት ጀምሮ እስከ 25 ኪሎ ሜትሮች ርቀው መጓዝ ይችላሉ። የንግሥት ኤልሳቤጥን ልደተ በዓል ተከትሎ ባለው ረጅም የሳምንቱ መጨረሻ ወደ ሪጂናል ቪክቶሪያ መጓዝ የተከለከለ ነው።የፊት ጭምብሎችበቤትዎ ውስጥ የ1 ነጥብ 5 ሜትሮች ርቀትን ለመጠበቅ በማይቻልባቸው ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር የፊት ጭምብል ለማጠለቅ ግዴታ አይኖርም።ትምህርት ቤቶችከዓርብ ጁን 11 ጀምሮ ትምህር ቤቶች ተማሪዎቻቸውን በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ማስተማር ይጀምራሉ። የምግብና መስተንግዶ ሥፍራዎችየምግብና መስተንግዶ ግልጋሎት ሰጪዎች ግልጋሎቶቻቸውን እስከ 100 ለሚደርሱ ደንበኞች መስጠት ሲችሉ ከ50 ላልበለጡ ተስተናጋጆች ተቀምጠው እንዲስተናገዱ ማድረግ ይችላሉ። ሌሎች አካላዊ እንቃስቃሴ ማካሄጃ፣ የዳንስ ሳሎንና የምሽት ክለቦች ዝግ ሆነው ይቆያሉ። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከተካሄዱ 28,000 የቫይረስ ምርመራዎች ውስጥ አንድ ግለሰብ ብቻ በቫይረሱ ተይዟል።የቪክቶሪያ ተጠባባቂ ፕሪሚየር ጄምስ ሜሊኖ በገደቡ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ንግዶች ተጨማሪ የ$8.36 ሚሊየን ድጎማ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

 


2 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now