የዩናይትድ ስቴትስ ግብርና ሚኒስቴር በወርኅ ሴፕቴምበር ባወጣው የ2022/23 የዓለም ስንዴ ምርት ውጤት ዝርዝር ኢትዮጵያ 5,700,000 ሜርትሪክ ቶን በማምረት ከዓለም 18ኛ ደረጃ ላይ መገኘቷን አመልክቷል።
በተያያዥነትም ቻይና 138,000,00 ሜትሪክ ቶን ስንዴን በማምረት ከዓለም የመጀመሪያውን ደረጃን የያዘች ሲሆን፤ ሩስያ 91,000,000 በማምረት አራተኛ፣ ዩናይትድ ስቴትስ 48,523,000 በማምረት አምስተኛ፣ አውስትራሊያ 33,000,000 በማምረት ሰባተኛ፣ ዩክሬይን 20,000,000 በማምረት ዘጠነኛ፣ ግብፅ 9,800,000 ሜትሪክ ቶን በማምረት 15ኛ ደረጃ ላይ ተመዝግበዋል።
ባለፈው የፈረንጆቹ ሴፕቴምበር ወር ምንም እንኳ የ2022/2023 የዓለም የስንዴ ምርት መጠን 78.392 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ይሆናል ተብሎ ቢገመትም፤ ከግምቱ በላይ የ4.32 ቶን ምርት ጭማሪ አሳይቷል።
ቀጣዩ የዓለም የስንዴ ምርት ውጤት ኦክቶበር 12 ቀን 2022 / ጥቅምት 2 ቀን 2015 ይፋ ይሆናል።
ክራሚያ
የፍንዳታ አደጋ ደርሶበት የነበረውና ሩስያን ከክራሚያ ጋር የሚያገናኘው ብቸኛው ከርች ድልድይ በከፊል ግልጋሎት ላይ መዋል ጀመረ።
ለሩሲያ የጦር መሳሪያዎችን ወደ ዩክሬይን ግንባር ለማመላለስ ጥቅም ላይ ይውል የነበረው ድልድይ የፍንዳታ አደጋ በገጠመው ወቅት አንድ ከባድ የጭነት መኪና መጋየቱንና የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ሩስያ አስታውቃለች።

Explosion causes fire at the Kerch bridge in the Kerch Strait, Crimea on October 08, 2022. Credit: Vera Katkova/Anadolu Agency via Getty Images
የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን
ኢትዮጵያን አስመልክቶ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዲመረምር በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ለተሰየመው በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተጠባቢዎች ኮሚሽን ለአንድ ዓመት በውክልናው እንዲቀጥል ይሁንታን አግኝቷል።
ውሳኔው በ21 ድጋፍ፣ 19 ተቃውሞና 7 ድምፀ ተዐቅቦ አልፏል።
ምክር ቤቱ ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሔደ ባለው ግጭት በሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች ዘንድ ማናቸውም ዓይነት የሰብዓዊ መብቶች አመፆችና ጥሰቶች፣ የዓለም አቀፍ ሕግን የመተላለፍ ድርጊቶች በአስቸኳይ እንዲገቱ ዳግም ጥሪ አቅርቧል።
ውክልናው ለአንድ ዓመት የተራዘመለት የሰብዓዊ መብቶች ቡድን በአምሳ - ሁለተኛው ስብሰባ የቃል ሪፖርት እንዲያስደምጥ፣ በአምሳ - አራተኛው ስብሰባ የፅሁፍ ሪፖርት እንዲያቀርብ፣ በሰባ - ስምንተኛው ስብሰባ ጠቅላላ ጉባኤው እንዲመክርበት መመሪያ ሰጥቷል።