ኳንታስ ክትባት ያልተከተቡ ዓለም አቀፍ መንገደኞችን እንደማያሳፍር አስታወቀ

*** የአየር መንገዱ የአገር ውስጥ ክትባትና በረራ ፖሊሲ ኦገስት ላይ ይፋ ይሆናል

News

A Qantas passenger plane takes off at Kingsford Smith Airport on July 11, 2021 in Sydney, Australia. Source: Getty

አውስትራሊያ በሯን ከፈረንጆች ገና በዓል በፊት ለዓለም አቀፍ በረራ ለመክፈት እየተዘጋጀች ባለችበት ወቅት የኳንታንስ አየር መንገድ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ አላን ጆንስ ለሁሉም የባህር ማዶ መንገደኞች የኮቪድ-19 ክትባት ያልተክተቡ መንገደኞችን ላለማሳፈር ዕቅድ መያዙን አስታውቀዋል።     

አየር መንገዱ የዓለም አቀፍ በረራውን ከተወሰኑ አውሮፕላን ማረፊያዎች ከዲሴምበር አጋማሽ ጀምሮ ይጀምራል። ኳንታስ ለበረራ ቅድሚያ ከሰጣቸው አገራት ውስጥ ጃፓን፣ ሲንጋፖር፣ ዩናይትድ ስቴትስና እንግሊዝ ይገኙበታል። 

አቶ ጆይስ የአውሮፕላን አስተናጋጆች፣ ፓይለቶችና የአውሮፕላን ማረፊያ ሠራተኞች እስከ ኖቬምበር 15 የተቀሩት ሠራተኞች በማርች 2022 መጨረሻ ሙሉ ክትባት ለማድረግ ግድ እንደሚሰኙ ተናግረዋል።  

ዋና ሥራ አሥፈፃሚው አየር መንገዱ በቅርቡ በረራ ከመጀመሩ በፊት ፖሊሲውን ይፋ እንደሚያደርግ ሲናገሩ "ኳንታስ ክትባት የተከተቡ ሰዎችን ብቻ እንደሚጭን ግድ የሚል ዓለም አቀፍ ፖሊሲ ይኖረዋል" ብለዋል። 

ይሁን'ጂ የአገር ውስጥ በረራን አስመልክቶ ገና ከውሳኔ ላይ ያልደርሱ መሆኑን ጠቁመው ኦገስት አካባቢ የአየር መንገዱን የአገር ውስጥ የክትባትና በረራ ፖሊስ ይፋ እንደሚያደርጉ ገልጠዋል። 

 

 


1 min read

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now