የንግሥቲቱ ማረፍ በይፋ በባኪንግሃም ቤተመንግሥት በኩል የተነገረው በአውስትራሊያ ሰዓት አቆጣጠር ዓርብ ማለዳ ላይ ነው።
የቤተመንግሥቱ መግለጫ "ንግሥቲቷ ዛሬ ከቀትር በኋላ ባልሞራል በሰላም አርፈዋል" ሲል ያስታወቀ ሲሆን፤ የቅርብ ቤተሰብ አባላቱም በነገው ዕለት ከባልሞራል ወደ ለንደን እንደሚመለሱ አመልክቷል።
የንግሥቲቱን ዕረፍት ተከትለው በዙፋናቸው በንጉሥነት የተተኩት የ73 ዓመቱ ቻርልስ የእናታቸውን ከዚህ ዓለም በሞት መለየት አስመልክተው በበኩላቸው ባወጡት መግለጫ የሐዘን ስሜታቸውንና ሁነቱን "ታላቅ የኃዘን ወቅት" ሲሉ ገልጠዋል።
መጠሪያቸውም ንጉሥ ቻርልስ ሳልሳዊ ይሆናል።
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚን ጨምሮ የበርካታ አገራት መሪዎች የሐዘን መግለጫ አውጥተዋል።