ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን አገር አቀፍ ምርጫ ለመጥራት ወደ መዲናይቱ ካንብራ እያመሩ ነው

*** የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ከስልጣናቸው ተገፍተው ወረዱ

News

Leader of the Opposition, Anthony Albanese (L) and Prime Minister of Australia, Scott Morrison (R) in the House of Representatives chamber at Parliament House. Source: Getty

ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ጠቅላይ እንደራሴው ዘንድ ቀርበው አገር አቀፍ ምርጫ ለመጥራት ወደ መዲናይቱ ካንብራ እያመሩ ነው። 

የምርጫው ቀን ሜይ 21 ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። 

አቶ ሞሪሰን መንግሥታቸው ድጋሚ እንዲመረጥ ሲጥሩ 55 - 46 ፐርሰንት በሕዝብ አስተያየት እየመራ ያለው የሌበር ፓርቲ አዲስ መንግሥት ለማቆም እየጣረ ነው።

ፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር

የፓኪስታን ተቃዋሚ ቡድን አባላት በጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ከሃን ላይ አመኔታ የለንም በሚል በአብላጫ የፓርላማ ድምፅ በመስጠት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከኃላፊነታቸው ገፍተው አውርደዋል።

የፓርላማው አፈ ጉባኤ 174 የምክር ቤት አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ አመኔታ እንደሌላቸው ድምፅ መስጠታቸውን አስታውቀዋል።  

የጠቅላይ ሚኒስትር ከሃን ደጋፊዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን መገፋት ተቃዋሚዎች ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ተመሳጥረው ነው በሚል  ዛሬ እሑድ  አገር አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ያካሂዳሉ።

News
Imran Khan. Source: Getty

የተቃዋሚዎቹን ቡድን በዋነኛነት የሚመራው የፓኪስታን ሙስሊም ሊግ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ሥፍራ ይይዛል። 

አቶ ክሃን ዓርብ ዕለት ባደረጉት ንግግር ዩናይትድ ስቴትስን አሌ ብለው ፊታቸውን ወደ ቻይናና ሩስያ በማዞራቸው ተቀናቃኞቻቸው በውጭ ፖሊሲ ምርጫቸው ቅሬታ ካደረባት አሜሪካ ጋር ተመሳጥረው ሊገፏቸው ማሰባቸውን ተናግረዋል። 


1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now