በእናታቸውን ዳግማዊት ኤልሳቤጥ ሕልፈተ ሕይወት ሳቢያ አልጋ ወራሽ የሆኑት የንጉሥ ቻርልስ ሳልሳዊ የንግሥና ሥነ ሥርዓት በይፋ ለንደን ውስጥ ተካሂዷል።
ንጉሥ ቻርልስ ርዕሰ ብሔር በሆኑባት አውስትራሊያ ውስጥም የሚካሔድ ይሆናል።
ለንደን በተካሔደበት ወቅትም ከ200 በላይ እድምተኞች ንጉሥ ቻርልስ በተገኙበት አዳራሽ በእማኝነትና ተጋባዥነት ተገኝተዋል።
የንግሥት ኤልሳቤጥ አስከሬን አሁን ባለበት ባልሞራል ተነስቶ ነገ እሑድ ወደ ኢደንብራ ሆሊሩድሃውስ ቤተመንግሥት ያመራል።
ከዚያም ለመንግሥታዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት ክንውን ማክሰኞ ዕለት ወደ ለንደን ያቀናል።