የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቻይናን ለመገዳደር በተቋቋመው የአራት አገራት ስትራቴጂያዊ ስብሰባ ላይ ለመታደም ሜልበርን ገቡ

*** አውስትራሊያ ውስጥ "ሙሉ ክትባት" መከተብ ማለት ሶስት ዙር ክትባቶችን መከተብ ማለት እንዲሆን ተወሰነ

News

U.S. Secretary Of State Antony Blinken waves as he disembarks from his plane upon his arrival at Melbourne Jet Base on February 9, 2022 in Melbourne, Australia. Source: Getty

የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ዓለም ላይ ተጋርጠው ያሉ ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ ለማለፍ እንደ ዩናይትድ ስቴትስና አውስትራሊያ ያሉ ቀና አመለካከት ያላቸው አገራት አብረው መሥራትን ግድ እንደሚል አሳሰቡ። 

አቶ ብሊንከን ዛሬ ሐሙስ ፌብሪዋሪ 10 ሜልበርን አውስትራሊያ የገቡት አውስትራሊያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ጃፓንና ሕንድን ባካተተውና ቻይናን ለመገዳደር በተቋቋመው የአራትዮሽ ስትራቴጂያዊ ስብሰባ ላይ ለመታደም ነው። 

 አቶ ብሊንከን ዛሬ ጠዋት ሜልበርን ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ተማሪዎችን በዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ አነጋግረዋል።  

አክለውም በአውስትራሊያና ዩናይትድ ስቴትስ መካከል ካለው መልክአ ምድራዊ ርቀት ባሻገር በዕሴቶቻቸውና ጥቅሞቻቸው መካከል ያሉ ልዩነቶች ጥቂት መሆናቸውን ገልጠዋል። 

"ሙሉ ክትባት" 

አውስትራሊያ ውስጥ "ሙሉ ክትባት" መከተብ ማለት ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሁሉ ሶስት ዙር ክትባቶችን መከተብ ማለት እንዲሆን የአውስትራሊያ ቴክኒካዊ የክትባት አማካሪ ቡድን ወሰነ።

ይህ የተገለጠው የብሔራዊ ካቢኔው በዛሬው ዕለት ያካሔደው ውሳኔ እንዳበቃ ነው። 

ሆኖም ውሳኔው እስካሁን ዓለም አቀፍ መንገደኞችን ገና አላካተተም።

በአሁኑ ወቅት ዕድሚያቸው 16 እና ከዚያ በላይ የሆኑ 93.9 ፐርሰንት አውስትራሊያውያን የሁለት ዙር ክትባቶችን ሲከተቡ ባለፉት 14 ሳምንታት 46.3 ፐርሰንቱ ሶስተኛ ዙር ክትባት ተከትበዋል። 

አዲሱ የሙሉ ክትባት ውሳኔ ወደ ሶስት ዙር ክትባት ከፍ ማለትን አስመልክቶ ኩዊንስላንድና ቪክቶሪያ ተመሳሳይ የሙሉ ክትባት ደረጃን በዓለም አቀፍ መንገደኞች ላይም ለመጣል አስበዋል።  

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ፕሪሚየር በበኩላቸው የክትባት ባለስልጣኑን ውሳኔ ተከትለው ከውሳኔ ላይ እንደሚደርሱ ጠቁመዋል። 

 

 

 

 


2 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now