የፌዴራል መንግሥቱ የነባር ዜጎች ሰንደቅ ዓላማ በአውስትራሊያ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እንዳይውለበለብ የእምቢታ ድምፅ አሳለፈ

*** "የነባር ዜጎች ሰንደቅ ዓላማም ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ነው" ሴናተር ማላንዲሪ ማክካርቲ

NAIDOC Week

Source: AAP

ከ65 ሺህ ዓመታት በላይ የአውስትራሊያ ሰፋሪና ባላገርነት ከኖቬምበር 8 - 15 ታስቦ በሚከበርበት የብሔራዊ ነባር ዜጎች (NAIDOC) ሳምንት ውስጥ የነባር ዜጎች ሰንደቅ ዓላማ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ውስጥ እንዲቆም የቀረበውን ጥያቄ የፌዴራል መንግሥቱ የእምቢታ ድምፅ በመስጠት ውድቅ አድርጎታል።

የነባር ዜጎች ሰንደቅ ዓላማ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ውስጥ ከአውስትራሊያ ሰንደቅ ዓላማ ጎን እንዲቆም ዕሳቤውን ዛሬ ዕለተ ማክሰኞ ያቀረቡት ከሌበር ፓርቲ ወገን ፓት ዶድሰንና ማላንዳሪ ማክካርቲ እንዲሁም ከግሪንስ ፓርቲ በኩል ሊዲያ ቶርፕ ናቸው።

ዕሳቤው 29 ለ28 በሆነ ውድቅ ሆኗል። 

የቤተሰብና ማኅበራዊ ግልጋሎቶች ሚኒስትር አን ራስተን "መንግሥት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ውስጥ ሊውለበለብ የሚገባው ብቸኛው ተገቢ ሰንደቅ ዓላማ ሁሉንም አውስትራሊያውያንን የሚወክለው የአውስትራሊያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ብቻ ነው ብሎ ያምናል" ብለዋል።

NAIDOC Week
Families and Social Services Minister Anne Ruston defending the government's decision on Tuesday. Source: APH/screenshot

"የነባር ዜጎች ሰንደቅ ዓላማም ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ነው" የያንዩዋዋ ሴት ሴናተር ማላንዲሪ ማክካርቲ አያይዘውም "በተሰረቀ መሬት ላይ ያለን መሆናንችንን ሁላችሁንም ልብ ላሰኝ እችላለሁ? የነባር ዜጎች ሰንደቅ ዓላማ በዓለም ላይ አንጋፋና ቀጣይ ባሕልን የሚወክል ነው"

NAIDOC Week
Labor Senator Malarndirri McCarthy waits for a press conference for the start of NAIDOC Week in Canberra. Source: AAP

“የኔ ሰዎች … ለሺህና ሺህ ትውልዶች እዚህ አሉ። የነባር ዜጎች ሰንደቅ ዓላማ እኛን ገላጭና የተቆራኘንበት ነው" በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።

 

 


1 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now