የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ለክራሚያ ድልድይ መጋየት የዩክሬይን የምስጢር አገልግሎቶች እጅ አለበት ሲሉ ከሰሱ።
አቶ ፑቲን ሩስያንና ዩክሬይንን የሚያገናኘውን ድልድይ ላይ ጉዳት በማድረስ ዩክሬይን "በሽብር ድርጊት" ተሳትፋለች ብለዋል።
አያይዘውም "ለዚህ ምንም ጥርጥር የለውም። ይህ ጠቀሜታው ወሳኝ የሆነን የሰላማዊ ሰዎች መሠረተ ልማትን ለማውደም ያለመ የሽብር ድርጊት ነው
"የተተለመው፣ ትዕዛዝ የተሰጠውና የተተገበረው በዩክሬይን ልዩ አገልግሎቶች ነው" ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ እሑድ ዕለት የተወነጨፈው የሩስያ ሚሳይል ጥቃት በዩክሬይን ደቡባዊ ምሥራቅ ከተማ በሆነችው ዛፖሪዝሂያ በሚገኝ አንድ አፓርትመንት ህንፃ ላይ ወድቆ የ13 ሰዎች ሕይወት ማለፉንና 89 ለመቁሰል አደጋ መዳረጋቸውን የዩክሬይን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
መከላከያ
የአውስትራሊያ መከላከያ ሚኒስትር ሪችድ ማርልስ የተወሰኑ የመከላከያ ፕሮጄክቶች ጊዜ ያለፋባቸው በመሆንና በዋጋቸው አለቅጥ መናር ሳቢያ ከእነ አካቴው ሊሰረዙ እንደሚችሉ አመላከቱ።
በያዝነው የወርኅ ኦክቶበር አዲስ የበጀት ትንተና መሠረት 28 የመከላከያ ፕሮጄክቶች በጋራ 97 ዓመታት ወደ ኋላ ቀርተዋል፤ 18 ፕሮጄክቶች ዋጋቸው በ6.5 ቢሊየን ዶላርስ አሻቅቦ ተገኝቷል።
በመሆኑም፤ የተወሰኑ ፕሮጄክቶች ሊታጠፉ እንደሚችሉና የመከላከያ ስትራቴጂ ክለሳ በሂደት ላይ ስለመሆኑ የመከላከያ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።