ቪክቶሪያ በድጋሚ የ19 ሰዎችን ሕይወት በኮሮናቫይረስ ሳቢያ አጣች

***ከሶማሌ ክልል መንግሥት በጎርፍ ለተጎዱ የአፋር ነዋሪዎች እርዳታ ተላከ

Victorian Premier Daniel Andrews.

Victorian Premier Daniel Andrews. Source: AAP

በዛሬው ዕለት ማክሰኞ ቪክቶሪያ ውስጥ የ19 ሰዎች ሕይወት በኮሮናቫይረስ ሲያልፍ 331 በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ሕይወታቸው ካለፈው ውስጥ አንዲት ሴት በ50ዎቹ፣ አንድ ወንድ በ70ዎቹ ፣ ስድስት ሴቶችና አራት ወንዶች በ80ዎቹ፣ አራት ሴቶችና ሶስት ወንዶች በ90ዎቹ ዕድሜ የነበሩ ናቸው። 

ከ19ኙ ሟቾቹ ውስጥ 14ቱ በአረጋውያን መጦሪያ ነዋሪ የነበሩ ናቸው።

ቪክቶሪያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የ19 ሰዎች ሲጠፋ የዛሬው ሁለተኛ ጊዜ ነው። ይህም ቪክቶሪያ ውስጥ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎችን ቁጥር ወደ 246 ሲያደርስ በአገር አቀፍ ደረጃ 331 ደርሷል።

የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት አፋር ውስጥ በደረሰው የተፈጥሮ ጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ነዋሪዎች የጤና ባለሙያዎችን አክሎ የተለያዩ እርዳታዎችን በዓይነት ልኳል።

የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ እንዳስታወቀው 300 ካርቶን የምግብ ዘይት፣350 ኩንታል ዱቄት፣566 ኩንታል ሩዝ 620 ብርድ ልብሶችና 520 የዝናብ መከላከያ ሸራዎች ለተጎዱ ወገኖች መርጃ ተልኳል።

 


1 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now