ዛሬ ሜይ 11 / ግንቦት 3 ማምሻውን በቻናል 7 ቴሌቪዥን አማካይነት በተካሔደው የመሪዎች ሶስተኛና የመጨረሻ ዙር የአገር አቀፍ ምርጫ ክርክር የሌበር መሪ አንቶኒ አልባኒዚ እስካሁን ድምፅ ለመስጠት ባልወሰኑ መራጮች አሸናፊ ተብለዋል።
መራጮቹ ከውሳኔ ላይ የደረሱት በጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰንና የተቃዋሚ ቡድን መሪ አንቶኒ አልባኒዚ መካከል የተካሔደውን ክርክር ተመልክተው ካበቁ በኋላ ነው።
የመራጮቹ የክርከር አሸናፊ ድምፅ የተውጣጣው ከተለያዩ የአውስትራሊያ ክፍለ አገራት ሲሆን፤ በአጠቃላይ የድምፅ ውሳኔ አቶ አልባኒዚ 50 ለ 34 በሆነ ግልፅ ብይን አሸናፊ ለመባል በቅተዋል።
በየክፍለ አገራቱ በተካሔዱት የድምፅ አሰጣጦች፤
ምዕራብ አውስትራሊያ - ሃስላክ
ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን 44 ፐርሰንት - አንቶኒ አልባኒዚ 44 ፐርሰንት - ከክርክሩ በኋላ ውሳኔ ላይ ያልደረሱ 25 ፐርሰንት
ኒው ሳውዝ ዌይልስ - ማኳሪ
ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን 25 ፐርሰንት - አንቶኒ አልባኒዚ 50 ፐርሰንት - ከክርክሩ በኋላ ውሳኔ ላይ ያልደረሱ 25 ፐርሰንት
ቪክቶሪያ - ቺዝሆልም
ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን 35 ፐርሰንት - አንቶኒ አልባኒዚ 52 ፐርሰንት - ከክርክሩ በኋላ ውሳኔ ላይ ያልደረሱ 13 ፐርሰንት
ደቡብ አውስትራሊያ - ቡዝቢይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን 32 ፐርሰንት - አንቶኒ አልባኒዚ 52 ፐርሰንት - ከክርክሩ በኋላ ውሳኔ ላይ ያልደረሱ 16 ፐርሰንት
ታዝማኒያ - ባስ
ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን 32 ፐርሰንት - አንቶኒ አልባኒዚ 52 ፐርሰንት - ከክርክሩ በኋላ ውሳኔ ላይ ያልደረሱ 16 ፐርሰንት
ኩዊንስላንድ - ሊሊ
ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን 41 ፐርሰንት - አንቶኒ አልባኒዚ 54 ፐርሰንት - ከክርክሩ በኋላ ውሳኔ ላይ ያልደረሱ 5 ፐርሰንት
ኖርዘርን ቴሪቶሪ - ሰለሞን
ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን 25 ፐርሰንት - አንቶኒ አልባኒዚ 50 ፐርሰንት - ከክርክሩ በኋላ ውሳኔ ላይ ያልደረሱ 25 ፐርሰንት ናቸው።