የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅት ዋና ፀሐፊ የንስ ስቶልተንበርግ 30 የድርጅቱ ሽርካ ጦር አባላት በሚቀጥለው ሳምንት የኑክሊየር ዝግጁነቱንና ብቃቱን ለመፈተሽ በረጅሙ የታቀደ ልምምድ ሊያካሂድ መተለሙን አስታወቁ።
የቃኪዳኑ ድርጅት የጦር ልምምድ ሰላምን ጠብቆ ማቆየት ላይ ያተኮረ የተለመደ ዓመታዊ ልምምድ መሆኑን ትናንት በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫቸው አስታውቀዋል።
በየዓመቱ የሚካሔደው ይኼው ልምምድ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን፤ ኑክሊየር የታጠቁ ተዋጊ ጄቶችን ያካትታል።
እንዲሁም፤ መደበኛ ተዋጊ ጄቶች፣ የቅኝትና የአየር ላይ ነዳጅ ሙሌት የልምምዱ አካል ይሆናሉ።
የጦር ቃልኪዳኑ ድርጅት የራሱ የሆነ ኑክሊየር መሳሪያዎች የሉትም።
የኑክሊየር ጦር መሳሪያዎቹ የሚገኙት በሶስቱ አባል አገራት ዩናይትድ ስቴትስ፣ እንግሊዝና ፈረንሳይ መከላከያ ኃይል ስር ነው።
ዝክረ መታሰቢያ
ዛሬ ረቡዕ ኦክቶበር 12 / ጥቅምት 1 በባሊ - ኢንዶኔዥያ በደረሰው የቦምብ ጥቃት 88 አውስትራሊያውያንን ጨምሮ የ202 ሰዎች ሕይወት የተቀጠፈበት 20ኛ ዓመት መታሰቢያ ነው።

Two-hundred and two people, including 88 Australians, died in the bombings on October 12, 2002 outside a pair of nightclubs, at the same site as the memorial, in the busy tourist area of Kuta. Credit: RICHARD A. BROOKS/AFP via Getty Images
ጥቃቶቹ የተፈፀሙት ከአል ቃይዳ ጋር ግንኙነት ባለው አንድ የሽብር ቡድን ነበር።
የጥቃቱ ሰለባዎች በኢንዶኔዥያና አውስትራሊያ በዕዝነ ኅሊና ታስበዋል።