ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዜ ሴፕቴምበር 22 / መስከረም 12 የዳግማዊት ኤልሳቤጥን ሕልፈተ ሕይወት ለመዘከር ብሔራዊ የሐዘን ቀን ሆኖ እንደሚውልና መሥሪያ ቤቶችም ዝግ እንደሚሆኑ አስታወቁ።
አቶ አልባኒዚ ብሔራዊ የሐዘን ቀኑን አስመልክቶ ለሁሉም የክፍለ አገርና ግዛት መሪዎች በደብዳቤ ጠይቀው ይሁንታን ያገኙ መሆኑንም አክለው ገልጠዋል።
የንግሥቲቱ የቀብር ሥነ ሥርዓት ሴፕቴምበር 19 / መስከረም 9 ለንደን ውስጥ እንደሚከናወንም ተነግሯል።