ቪክቶሪያ የ2006 የጋራ ብልፅግና ጨዋታዎች አስተናጋጅ ሆና ተመረጠች

*** ስኮት ሞሪሰን 1.3 ሚሊየን የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ዕቅድ አለኝ ሲሉ፤ አንቶኒ አልባኒዚ ለአዕምሮ ጤና ድጋፍ እንደሚያደርጉ አስታወቁ።

News

A general view of fireworks during the Closing Ceremony for the Gold Coast 2018 Commonwealth Games at Carrara Stadium on April 15, 2018 on the Gold Coast. Source: Getty

ቪክቶሪያ የ2026 የጋራ ብልፅግና ጨዋታዎችን ለማስተናገድ በጋራ ብልፅግና ፌዴሬሽን ተመረጠች።

ዝግጅቶቹ በአብዛኛው በሪጂናል ቪክቶርያ የሚካሔዱ ይሆናል። 

 የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ የስፖርት ውድድሮቹ ቤንዲጎ፣ ባላራት፣ ጂሎንግ እና ጊፕስላንድ እንደሚከናወኑ ገልጠዋል።  

እንዲሁም ዋነኛ ስፖርታዊ ውድድሮች፣ የሥነ ሥርዓቱ መክፈቻና መዝጊያዎች ሜልበር ውስጥ ይካሄዳሉ። 

 ሥራ ፈጠራ

ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት 1.3 ሚሊየን የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ማቀዳቸውን ገለጡ። 

የአቶ ሞሪሰን ጥምር መንግሥት የፍብረካ፣ የእጅ ሙያ የሥራ ቦታ ስልጠናና ክህሎትን ማሳደግ ላይ እንደሚያተኩር አመላክቷል።

News
Prime Minister Scott Morrison has taken aim at Opposition leader Anthony Albanese's economic credentials on day two of the election campaign. Source: AAP

የሥራ አጥነት መጠን በዚህ ዓመት መጨረሻ ወደ 3.75 ፐርሰንት ዝቅ እንደሚል ይጠበቃል። 

አቶ ሞሪሰን አሁን ተከስቶ ያለውን የሠራተኞችን እጥረት ለመቅረፍ ተጨማሪ ሠራተኞች ከባሕር ማዶ እንዲመጡ በር ይከፍቱ እንደሁ ተጠይቀው፤ በጀት ውስጥ ከሠፈረው 160,000 በላይ ተጨማሪ ባሕር ማዶኞች ወደ አውስትራሊያ እንዲዘልቁ እንደማይደረግ ተናግረዋል። 

የቴሌጤና ፕሮግራም 

የአውስትራሊያ ሌበር ፓርቲ በገጠራማ አውስትራሊያ ለሚኖሩ አውስትራሊያውያን በያዘው የጤና ፕሮግራም መሠረት የስነ አዕምሮ ግልጋሎት እንዲያገኙ የቴሌጤና ፕሮግራም ማካሄጃ የሚውል 31 ሚሊየን ዶላርስ መመደቡን የተቃዋሚ ቡድን መሪ አቶ አንቶኒ አልባኒዚ ዛሬ ታዝማኒያ ባካሄዱት የምርጫ ዘመቻ ወቅት አስታውቀዋል። 

News
Opposition Leader Anthony Albanese speaks to the media on day two of the 2022 federal election campaign, in Longford, Tasmania. Source: AAP

አያይዘውም፤ የቴሌጤና ፕሮግራሙ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የነበረውን የ50 ፐርሰንት ድጎማ የሞሪሰን መንግሥት በመክላቱ ያንን ክፍተት ለሟሟላትና ግልጋሎቶቹን በርካሽ ማካሔድ እንዲያስችል ለማድረግ መሆኑን ገልጠዋል። 

በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ውስጥ 450,000 አውስትራሊያውያን የቴሌጤና ግልጋሎቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ጥናቶች የሚያመልክቱ እንደሆነም አቶ አልባኒዚ አስረድተዋል። 

 

 


2 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now