ከለውጡ በኋላ በፕሮጀክቱ ላይ በተወሰደው የማስተካከያ እርምጃ በግድቡ ውስጥ መተከል የነበረባቸው የውሃ ማስተላለፊያ የብረታ ብረት ሥራዎችን ተጠናቀው፤ የግድቡን የመካከለኛው ክፍል ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ 600 ሜትር እንዲሁም ግራና ቀኙን 611 ሜትር ማድረስ መቻሉ ተገልጿል፡፡
ከሦስት ዓመት በፊት ለዘመናት ከባህር ጠለል በላይ በአምስት መቶ ሜትር ከፍታ ላይ ይፈስ የነበረው የአባይ ወንዝ፤ ዛሬ ለሦስተኛ ዙር በግድቡ አናት ላይ የፈሰሰው ከባህር ጠለል በላይ በስድስት መቶ ሜትር ከፍታ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት የግድቡ ግራና ቀኝ ጠርዝ ከባህር ጠለል በላይ ስድስት መቶ አርባ አምስት ሜትር የደረሰ ሲሆን፤ የግድቡ የሲቪል ሥራዎች ግንባታ 95 በመቶ፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ፍብረካና ተከላ 61 በመቶ እንዲሁም የብረታ ብረት ሥራ 73 በመቶ፣ አጠቃላይ አፈፃፀሙ ደግሞ 83 ነጥብ 3 በመቶ ደርሷል፡፡
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከፍታ ከመሬት 145 ሜትር ሲሆን፤ እርዝመቱ ደግሞ 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ይሆናል፡፡
የዋናው ግድብ ውፍረት የግድቡ ግርጌ ላይ 130 ሜትር፥ የግድቡ ጫፍ ወይም የላይኛው ክፍል ደግሞ 11 ሜትር ነው።
በግድቡ ግንባታ ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎችም የደስታ ሥሜታቸውን ገልፀዋል።
በበጀት ዓመቱ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኹለት ዩኒት ኃይል ማመንጨት እንዲጀምር ለማድረግ የያዘው እቅድ መሳካቱን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሶስተኛውን ዙር የውኃ ሙሌት አስመልክተው "በቃላችን መሠረት፣ ማንም ላይ ጉዳት ሳናደርስ እነሆ 3ኛውን ዙር ውኃ ሙሌት በታሰበው ጊዜ ማጠናቀቅ ስለቻልን የዓባይ ልጆች ሁሉ እንኳን ደስ ያለን!!" ብለዋል።
የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንም በበኩላቸው በቲወተር ገፃቸው "የእንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን" መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዓባይ ለሶስተኛ ጊዜ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አናት ላይ መፍሰስ ጀመረ
የዓባይ ወንዝ ዛሬ ለሶስተኛ ዙር በግድቡ አናት ላይ የፈሰሰው ከባህር ጠለል በላይ በስድስት መቶ ሜትር ከፍታ ነው፡፡

A general view of the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD). Credit: Amanuel SILESHI / AFP
Share
Published
Updated
By Stringer Report
Source: SBS
Share this with family and friends