የአውስትራሊያ የመከላከያ ሚኒስትር በአውስትራሊያና ቻይና መካከል ንግግር ሊካሔድ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ ገለጡ

*** የቻይናና የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትራት በሁለቱ አገራት መካከል ተፈጥረው ላሉት ውጥረቶች አርጋቢ ብልሃቶችን ለማፈላለግ የተነጋገሩ ቢሆንም ችግር ፈቺ እልባት ላይ ሳይደርሱ ቀርተዋል።

News

China’s Minister of National Defense General Wei Fenghe (centre) speaks to an aide during the Opening of the International Institute for Strategic Studies. Source: EPA / HOW HWEE YOUNG/EPA

የአውስትራሊያ መከላከያ ሚኒስትር ሪችድ ማርልስ በሲንጋፖር ዓለም አቀፍ የመከላከያ ሚኒስትራት ጉባኤ ላይ በተካሔደ የትውውቅ ሥነ ሥርዓት ከቻይና አቻቸው ጄኔራል ዌይ ፌንግሂ ጋር እጅ ለእጅ በመጨባበጥ ተዋውቀዋል። 

የቻይናና አውስትራሊያ ግንኙነት ቅዝቃዜ ከገባው ከሁለት ዓመታት በኋላ የሁለቱ አገራት የመከላከያ ሚኒስትሮች ለስብሰባ በአንድ ላይ ሲታደሙ ይህ የመጀመሪያው ጊዜ ነው።

መከላከያ ሚኒስትር ማርልስ ከጄኔራል ዌይ ጋር ያደረጉት ግንኙነት ከእጅ ለእጅ መጨባበጥ የዘለለ የትውውቅ ሥነ ሥርዓት እንጂ የሰከነ የሁለትዮሽ ንግግር ባለመሆኑ ከዚያ በላይ አግኖ ማየት እንደማያሻ ተናግረዋል። 

ይሁንና ሲንጋፖር ሻንግራይ-ላ እየተካሔደው ያለው ጉባኤ አንድ ተጨማሪ ቀን ስለሚቀረው ከቻይናው አቻቸው ጋር ምናልባትም በወጉ ተገናኝቶ የመነጋገር ዕድል ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል። 

አቶ ማርልስ እንዲህ ባለ ውስብስብ ጊዜ ዓለም አቀፍ ግንኙነት "በረጋ፣ ሙያዊ በሆነና መከባበርን በተላበሰ" መልኩ ሊካሄድ እንደሚገባ አሳስበዋል። 

ሆኖም አውስትራሊያ ብሔራዊ ጥቅሞቿን አስመልክቶ ሉላዊ ሥርዓተ ደንብን በተከተለ መንገድ እንዲከወን ለማስደረግ ወደ ኋላ እንደማትልም ገልጠዋል። 

 

በሌላም በኩል መከላከያ ሚኒስትሩ ከፈረንሳዩ አቻቸው ሰባስቲያን ሌኮርኑ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል። 

 

ሁለቱ ሚኒስትራት ንግግራቸው አዎንታዊነት የመላውና ባለፈው የስኮት ሞሪሰን መንግሥት ወቅት በባሕር ሰርጓጅ መርከብ ውል ስረዛ ሳቢያ ሻክሮ የነበረውን ግንኙነት በአዲስ መልክ ለመጀመርም ቃል ተለዋውጠዋል።  

News
Source: R.Marles

.ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ምንም እንኳ ቻይና በኢንዶ-ፓስፊክ ቀጣና ይበልጡኑ ግፊቷ እየጠነከረ ያለ ቢሆንም በዋሽንግተንና ቢጂንግ መካከል ተፈጥረው ያሉትን ውጥረቶች ለማርገብና ግጭት እንዳይፈጠር ከወዲሁ ለመግታት ጥረት እንደምታደርግ ተናግረዋል። 

 

ሁለቱ የዓለም ታላላቅ ባለ ምጣኔ ሃብት አገራት በተለይም በታይዋን፣ በቻይና የሰብዓዊ መብቶች ሬኮርድና የደቡብ ቻይና ባሕር እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ በመካከላቸው ውጥረቶች ሰፍነው አሉ። 

News
China's Defence Minister Wei Fenghe (R) talks to US Defense Secretary Lloyd Austin (L), Singapore's Defence Minister Ng Eng Hen (2nd L) shakes hands with Marles Source: Getty

አቶ ኦስቲን በቻይናና ዩናይትድ ስቴትስ መካከል ተፈጥረው ያሉትን ውጥረቶች አርጋቢ ብልሃቶችን ለማፈላለግ ከጄኔራል ዌይ ጋር ዓርብ ዕለት ተገኛኝተው ለአንድ ሰዓት ያህል  የተነጋገሩ ቢሆንም ችግር ፈቺ እልባት ላይ ሳይደርሱ ተለያይተዋል።

 


2 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now