SKIP TO MAIN CONTENT

የቪክቶሪያ ዕለታዊ የኮሮናቫይረስ ቁጥር ወደ 37 ወረደ

*** ሕወሓት በትግራይ ክልላዊ ምርጫ በ98.2 ፐርሰንት ማሸነፉ ተነገረ

Amharic News 12 September 2020
Victorian Premier Daniel Andrews Source: AAP

1 min read

Published

By Kassahun Seboqa Negewo


Skip to article content

ባለፉት 24 ሰዓታት ቪክቶሪያ ውስጥ 37 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲጠቁ ስድስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በቫይረሱ የተጠቁት ሰዎች ቁጥር ከጁን 25 ወዲህ ዝቅተኛው ነው።

ይህም የ14 ቀናቱን አማካይ የቫይረስ መጠን በሜልበርን 61.6 በሪጂናል ቪክቶሪያ 4.3 እንዲደርስ ማድረጉን ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ ተናግረዋል።

ስድስቱም ሕይወታቸውን በቫይረሱ ሳቢያ ያጡት የአረጋውያን መጦሪያ ነዋሪዎች የነበሩ ሲሆን፤ ሁለት ሴቶችና አንድ ወንድ በ80ዎቹ፣ ሁለት ሴትና ስንድ ወንድ በ90ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የነበሩ ናቸው።

ተጨማሪው ሞት ቪክቶሪያ ውስጥ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 716 አድርሷል።

በአሁኑ ወቅት በኮቪድ-19 ተይዘው ያሉ 1251 ሲሆኑ 126 ሆስፒታል ተኝተው የሚታከሙ፣ ዘጠኝ ፅኑ ሕሙማን ክፍሎች ሕክምና የሚከታተሉና ስድስት በሰው ሠራሽ መተንፈሻ እየተነፈሱ ያሉ ናቸው። 

ምርጫ

በትግራይ ክልል ጳጉሜን 4 በተካሔደው ክልላዊ ምርጫ ሕወሓት አሸናፊ መሆኑን የክልሉ ምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል።

በውጤቱም፤

ሕወሓት - 98.2 %

ባይቶና - 0.8 %

ውናት - 0.71 %

ሳወት - 0.27 %

አሲምባ - 0.0.1 % ድምፅ ማግኘታቸውን የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ለብዙሃን መገናኛ ገልጠዋል።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now