ቪክቶሪያ ውስጥ ተጨማሪ 278 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተጠቁ - ስምንት ሕይወታቸውን ተነጠቁ

*** ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ያሉ ሰዎች ቁጥር ከ13 ሺ አልፏል - 463 ሕይወታቸውን አጥተዋል

AUG 24: Victoria records the lowest daily increase in cases since July 5

AUG 24: Victoria records the lowest daily increase in cases since July 5 Source: AAP

ቪክቶሪያ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 278 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሕይወታቸውን ሲያጡ ስምንት ለሞት ተዳርገዋል።

በትናንትናው ዕለት ቪክቶሪያ የ21 ሰዎቿን ሕይወት ስታጣ 410 በኮሮናቫይረስ ተጠቅተውባታል።

የዛሬው ቁጥር ከጁላይ 20 ወዲህ አዲስ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አሽቆልቁሎ የታየበት ነው።

የስምንቱ ስዎች ሕልፈተ ሕይወት የቪክቶሪያን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 275 ሲያደርሰው አገር አቀፉን ወደ 360 ከፍ አድርጎታል።

ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ በዛሬው ዕለት ሕይወታቸውን በኮሮናቫይረስ ያጡቱ ስምንቱ ሰዎች የአረጋውያን መጦሪያ ነዋሪዎች እንደነበሩ ገልጠዋል።

አያይዘውም፤ ከሟቾቹ ውስጥ አንዲት ሴት በ50ዎቹ፣ ሁለት ወንዶች በ70ዎቹ፣ ሁለት ሴቶች በ80ዎቹ፣ ሁለት ወንዶች በ80ዎቹ እንዲሁም አንድ ወንድ በ90ዎቹ የነበሩ መሆኑን አስታውቀዋል።  

ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ ኢትዮጵያ ውስጥ እስከ ነሐሴ 6 - 20212 በነበሩት 24 ሰዓታት ውስጥ 943 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 23 ሕይወታቸው አልፏል።

በአሁኑ ወቅት በአገር አቀፍ ደረጃ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተው ያሉ ሰዎች ቁጥር 13 ሺህ 619 ደርሷል። 463 ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በጠቅላላው በቫይረሱ ተይዘው ከነበሩት 25 ሺህ 118 ሰዎች ውስጥ 11 ሺህ 34 አገግመዋል። 


Share

1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service