የሌበር ፓርቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሶስት አሠርት ዓመታት በላይ በሊብራል ፓርቲ ስር የቆየውን የኒው ሳውዝ ዌይልስ ምክር ቤት ወንበር አሸነፈ

*** ጆ ባይደንና ቭላድሚር ፑቲና ዩክሬይንን አስመልክተው ዳግም በስልክ ተነጋገሩ

Kiongozi wa NSW Dominic Perrottet, azungumza na waandishi wa habari akiwa na mgombea wa Liberal Tim James, nje ya kituo chakupigia kura

Kiongozi wa NSW Dominic Perrottet, azungumza na waandishi wa habari akiwa na mgombea wa Liberal Tim James, nje ya kituo chakupigia kura. Source: AAP

የፔሮቴይ መንግሥት የኒው ሳውዝ ዌይልስ ቢጋ የምክር ቤት ወንበርን በሟሟያ ምርጫ ድል ተነስቶ ለሌበር አሳልፎ ሰጥቷል። 

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ፕሪሚየር ዶሞኒክ ፔሮቴይም መንግሥታቸው ወንበሩን ማጣቱን አምነው ተቀብለው የሌበር ቢጋ ተወዳዳሪውን ዶ/ር ማይክል ሆላንድን እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል።

ይህም ሆኖ ግና የቢጋ ሊብራል ዕጩ ተወዳዳሪዋ ፊዮና ኮትቮጅስ በፖስታ የተሰጡ ድምፆች ቆጠራ የሚጀምረው ዛሬ ቅዳሜ በመሆኑ የዚያ ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ ድል ተነስቻለሁ ብዬ አልቀበልም በማለት የሌበር ተቀናቃኛቸውን እስካሁን እንኳን ደስ አለዎት አላሉም።

News
Source: NSW Labor

 

 

የመጨረሻው ይፋ የድምፅ ቆጠራ ውጤት በአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን ሳይገለጥ የዶ/ር ማይክል ሆላንድ አሸናፊነት የታመነው በይፋ ተቆጥረው ከተመዘገቡት 25 ፐርሰንት ድምፆች ውስጥ 13 ፐርሰንት ድምፆች ከሊብራል ይልቅ ለሌበር የተሰጡ በመሆኑ ነው። .

የቢጋ የምክር ቤት ወንበር ዕጩዎችን ማስመረጥ ከተጀመረበት 1988 ጀምሮ ከሊብራል ፓርቲ እጅ ሳይወጣ የቆየ ነው። 

የሌበርን ለመጀመሪያ ጊዜ አሸናፊነት ተከትሎ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ሌበር ፓርቲ መሪ ክሪስ ሚንስ "የኒው ሳውዝ ዌይልስ ፕሪሚየር ያን መልዕክት ማድመጥ ያሻዋል። መንግሥት አቅጣጫውን ሊቀይር ይገባዋል" ብለዋል። 

የምዕራብ ሲድኒ ስትራትፊልድ የምክር ቤት ወንበርን በአጋር ፓርቲና የግል ተወዳዳሪ ድምፆች ታግዘው የሌበር ፓርቲ ዕጩ ተወዳዳሪ ጄሰን ያት ሴን ሊ የቀድሞዋን የሌበር ፓርቲ ተቃዋሚ ወንበር መልሰው ለመያዝ እየመሩ ይገኛሉ። 

ኒኮል ኦቨርሆልም በበኩላቸው ቀደም ሲልም በናሽናልስ ፓርቲ ስር ያለውን የሞናሮ ምክር ቤት ወንበር ሳያስነጥቁ በአሸናፊነት እየመሩ ይገኛሉ።

የቀድሞዋ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ፕሪሚየር የምክር ቤት ወንበር የነበረው ዎሉግቢ በተተኪያቸው የሊብራል ዕጩ ቲም ጄምስ አሸናፊነት ስር ውሏል።

ባይደን - ፑቲን

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን የሩሲያን ከ100,000 በላይ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬይን ድንበር ማስጠጋት አስመልክተው ዳግም ከፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ተነጋገሩ። 

ሩስያ ዩክሬይንን የምትወር ከሆነ ዩናይትድ ስቴትና አጋሮቿ "ወሳኝና ፈጣን" እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ተናግረዋል።  

ባይደንና ፑቲን ከአንድ ሰዓት በላይ በስልክ ተነጋግረዋል።  

የባይደን ብሔራዊ ፀጥታ አማካሪ ጄክ ሱሊቫን ሩስያ የቤጂንግ የክረምት ኦሎምፒክ ፌብሪዋሪ 20 ከማብቃቱ በፊት ዩክሬይንን እንደምትወር የዩናይትድ ስቴትስ መረጃ እንደሚያመለክት ገልጠዋል።  

ይህ በእንዲህ እንዳለም የዩክሬይን ጠቅላይ ሚኒስትር ዲኒስ ሽምይሃል ዩክሬናውያን ከመደናገጥ ይልቅ በመንግሥትና ጦር ሠራዊታቸው ላይ እምነት እንዲያሳድሩ አሳስበዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክታቸው መጥፎው ነገር መደናገጥን የሚፈጥረው "የተሳሳተ መረጃ" ስርጭት እንደሆነ በመግለፅ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት ከሩስያ በኩል ይቃጣል ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል። 

ሆኖም አውስትራሊያን ጨምሮ ዩናይትድ ስቴትስ፣ እንግሊዝና የአውሮፓ አገራት የኤምባሲ ሠራተኞቻቸው ኪየቭን ለቅቀው እንዲወጡ እያደረጉ ነው። 

 

 

 

 


2 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now