ቋሚ ሲኖዶሱ "የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልከቶ እየተደረጉ ያሉ ሁለገብ ተጽእኖዎችን" በጽኑ ይቃወማል- ኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን

የምሥራቁ ዓለም አገራት ላይ በማግባባት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጫና በማሳደር እንዲቀበሉ የጥፋት ልማዳቸውን እንዲጋሩ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉትን "ድብቅና ግልጽ እንቅስቃሴዎች" ቋሚ ሲኖዶስ በጽኑ እቃማለሁ ሲል አቋሙን አስታወቀ።

EOTC Logo.png

Credit: EOTC

ቋሚ ሲኖዶሱ ሰኞ የካቲት 4 ባወጣው መግለጫ፤ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልከቶ እየተደረጉ ያሉ ሁለገብ ተጽእኖዎችንና መመሪያ የማስለወጥ ማግባባቶችን በጽኑ እንደሚቃወም ገልጿል።

“ይህ ግብረ ርኵሰት በዘመናችን ተቀባይነት እንዲኖረው የሚደረጉ ሁለገብ ማግባባቶች፣ ተጽዕኖዎችና ተያያዥነት ያላቸው ስምምነቶች በአገራችን መንግሥት ተቀባይነት አግኝተው እንዳይፈጸሙ” ሲልም ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ አሳስቧል።

 ከተለያዩ ምንጮች ያገኘውን መረጃ ዋቢ ያደረገው ቋሚ ሲኖዶሱ፤ ግብረ ሰዶማዊነትንና ተያያዥነት ያላቸውን ተግባራት የንግድ፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የፍትሕና የሰብዓዊነት ግንኙነቶች አካል በማድረግ በቃላትና በዓረፍተ ነገሮች ውስጥ አስርጎ በማስገባት አሣሪ ስምምነቶች እንዲፈጸሙ ለማድረግ ያለው ሂደት በአፋጣኝ እንዲፈተሽ ጠይቋል።

እንዲሁም፤ የሀገሪቷ መንግሥት ብሎም የአፍሪካ መንግሥታት የአህጉሪቷን ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ዕሴቶች አስጠብቀው እንዲቀጥሉ በማለትም ጥሪውን አቅርቧል።

 በስምምነቱ ሰነድ ጤናማ መስለው የሠረፁ ዐረፍተ ነገሮች ውስጥ በጾታና ሥርዓተ ጾታ መብት፣ የሥርዓተ ጾታ ትምህርት ጋር በማያያዝ ጾታን በቀዶ ጥገና የመቀየር ውርጃ ልቅ የሆነ የተመሳሳይና ተቃራኒ ጾታ ግንኙነትን መፍቀድ፣ግለሰቦችን እና ማኅበረሰብን መረን በማድረግ ውስብስብ ለሆነ ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ ችግሮች የሚዳርጉ ናቸውም ብሏል።

ይህን አስመልክቶ የሚደረጉ ስምምነቶች የሀገሪቷን ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ዕሴት የሚጥሱ መሆኑ ታውቆ የፈዴራል መንግሥትም ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲከታተለው አሳስቧል።

ስለሆነም ግብረ ሰዶምን እና ተያያዥ የጾታ ሥርዓትን የሚበርዙ ተግባራት በሙሉ ሀገሪቷ በሃይማኖት፣ በሕግ፤ በማኅበራዊ ዕሴቶቿና በሥነ ምግባር መመሪያዎቿ የማትቀበላቸው ጉዳዮችና ልምምዶች ስለሆኑ በማናቸውም ይፋዊ ግንኙነቶች እንደማይቀበላቸውም ቋሚ ሲኖዶሱ አክሏል።

በምዕራቡ ዓለም የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነቶች ከሰብዓዊ መብቶች ጋር ተያይዘው የሚታዩ ናቸው።


Share

Published

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
ቋሚ ሲኖዶሱ "የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልከቶ እየተደረጉ ያሉ ሁለገብ ተጽእኖዎችን" በጽኑ ይቃወማል- ኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን | SBS Amharic