የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚደንትና ምክትል ፕሬዚደንቶችን መረጠ

*** ሳዑዲ አረቢያ በአንድ ቀን 81 ሰዎች ላይ የሞት ቅጣት ፈጸመች

News

DPM Demeke Mekonnen (L), PM Abiy Ahmed (C), and Adem Farah (R). Source: Getty

ከምሥረታው በኋላ "ከፈተና ወደ ልዕልና" በሚል መሪ ቃል የመጀመሪያ ጉባኤውን ያካሔደው የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚደንትና ምክትል ፕሬዚደንቶቹን መርጧል።

በምርጫ ሂደቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፓርቲው ፕሬዚደንት፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና አቶ አደም ፋራህ ምክትል ፕሬዚደንቶች ሆነው ተመርጠዋል። 

በዚሁ የፓርቲው መሪዎች ምርጫ በተከናወነበት በትናንትናው ዕለት ሁሉንም ኢትዮጵያውያን አቃፊ የሆነ ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ መፅደቁን የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ አስታውቀዋል። 

 

ዶ/ር ቢቂላ አክለውም፤ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ ጉዳይ፣ የውጭ ጉዳይና የዲፕሎማሲ ጉዳዮችን አካትቶ በያዘው ፕሮግራም ላይ ውይይት መካሔዱን ገልጠዋል።

 

የሞት ቅጣት በሳዑዲ

ሳዑዲ አረቢያ የተለያዩ ወነጀሎችን ፈፅመዋል በተባሉ 81 ሰዎች ላይ የሞት ቅጣት እርምጃ አካሔደች።

የሞት ቅጣት ትግበራው ቁጥር ብዛት ቀደም ሲል በሳዑዲ ዘመናዊ ታሪክ ያልተመዘገበ ነው። 

በመንግሥት የሚተዳደረው የሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የሞት ቅጣቱ የተፈፀመባቸው ግለሰቦች "በወንዶች፣ ሴቶችና ሕፃናት ግድያን አካትቶ በተለያዩ ወንጀሎች ይሙት በቃ የተፈረደባቸው" ናቸው ተብሏል። 

ኤጀንሲው አያይዞም፤ የተወሰኑት የአል ቃይዳ፣ እስላማዊ ስቴት አባላትና የየመን ሆቲ አማፅያን ደጋፊዎች ነበሩ ብሏል። 

ሳኡዲ ከዚህ ቀደም በ2016 ሳኡዲ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ ያካሄዱ አንድ የሺዓ መሪን ጨምሮ 47 ሰዎች ላይ በአንድ ቀን የሞት እርምጃ ፈፅማለች።

 


1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now