ቪክቶሪያ ከነገ ሴፕቴምበር 14 ጀምሮ የመጀመሪያ ደረጃ የቤተሰብ ጥየቃ፣ አካላዊ እንቅስቃሴና የሰዓት ዕላፊ ገደብ ለውጥ ታደርጋለች

*** የቪክቶሪያ መንግሥት ለንግድ ተቋማት የ$3 ቢሊየን ድጎማ ፕሮግራም ዘረጋ

Amharic News 13 September 2020

People exercise at Albert Park Lake in Melbourne. Source: AAP Image/Michael Dodge

የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ እሑድ ሴፕቴምበር 6 - 2020 የሜልበርንና ሪጂናል ቪክቶሪያ የኮሮናቫይረስ ገደቦች ማላሊያ ፍኖተ ካርታን ይፋ ባደረጉበት ወቅት የሜልበርን ደረጃ 4 ገደቦች እስከ ሴፕቴምበር ወር መጨረሻ የተራዘሙ ሲሆን፤ እስከ ሴፕቴምበር 13 ከ8pm-5am ተጥሎ ያለው ሰዓት ዕላፊ ገደብ ከሴፕቴምበር 14 ጀምሮ ከ9pm-5am ተራዝሞ ይቀጥላል።  

ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የማንሰራሪያ ፍኖተ ካርታ የሜልበርንና ሪጂናል ቪክቶሪያ ገደቦች አነሳስ ለየቅልና የተለያዩ ደረጃዎች አሏቸው።

ዕቅዱ ግብር ላይ የሚውለው ደረጃ በደረጃ ነው።

  • በመጀመሪያው ደረጃ ላጤዎችና ላጤ እናቶችን ቤታቸው በመዝለቅ አንድ ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል መጥቶ ሊጎበኛቸው ይችላል
  • አሁን ያለው የአንድ ሰዓት አካላዊ እንቅስቃሴ በደረጃ አንድ በቀን ወደ ሁለት ሰዓት ከፍ ይላል። ይህም በተከታታይ ለሁለት ሰዓታት አለያም በፈርቃ ለሁለት ጊዜ ሙሉ ሰዓት አካላዊ እንቅስቃሴ ማካሄድ ይቻላል
  • አካላዊ እንቅስቃሴውን በሚያደርጉበት ወቅትም አብሮዎት ከሚኖር ወይም ከቤት ውጭ ካለ አንድ ሰው ጋር መሆን ይችላሉ   
  • ምክንያታዊ ፈቃድ ካላቸው ጉዳዮች (ሥራ፣ ትምህርትና ጤና) በስተቀር ከ5 ኪሎ ሜትሮች ርቆ መሔድ አይቻልም
  • ትምህርት ቤቶች በርቀት ትምህርታቸው ይቀጥላሉ
  • አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለመሸመት ከአንድ ቤተሰብ በቀን አንድ ሰው ወደ ገበያ መሔድ ይችላል
  • ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ ያሉ ከቤት ውጪና የሸመታ ሥፍራዎች ላይ የፊት ጭምብሎችን ማጥለቅ ግድ ይሰኛሉ 
ደረጃ አንድ - ሪጂናል ቪክቶሪያ

  • የሪጂናል ቪክቶሪያ ነዋሪዎች ከሴፕቴምበር 13 ክምሽቱ 11:59pm ጀምሮ ላጤዎችና ላጤ እናቶችን ቤታቸው በመዝለቅ ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል መጥቶ ሊጎበኛቸው ይችላል። 
  • ከቤት ውጪም እስከ አምስት ሰዎች በመናፈሻ፣ የባሕር ዳርቻ ከሁለት ቤተሰብ ባልበለጠ መገናኘት ይችላሉ።
  • ለሪጂናል ቪክቶሪያ የውጪ መጫዎቻ ሥፍራዎች ክፍት ይሆናሉ። እንዲሁም በውጪ እስከ አምስት ምዕመናንና አንድ የእመነት መሪን ጨምሮ ሃይማኖታዊ ግልጋሎቶችን ማከናወን ይችላሉ። 
ሴፕቴምበር 28 ከመዳረሱና ወደ ደረጃ ሁለት ሽግግር ከመደረጉ በፊት በጤና ባለሙያዎች ቡድን የቫይረሱ መስፋፋት ደረጃ ይገመገማል። 

በደረጃ ሁለት ሽግግር ወቅት ሜልበርን ውስጥ የኮንስትራክሽን፣ ማምረቻ ፋብሪካዎች፣ የመናፈሻ ስነ-ገጽና በተናጠል የሚሰሩ ሠራተኞችን አካትቶ ወደ 100,000 የሚደርሱ ወደ ሥራ ገበታቸው ይመለሳሉ።

ችርቻሮና መስተንግዶን ከመሳሰሉ ከሌሎች ንግድ ተቋማት ጋር አሁን እስከ ሴፕቴምበር ተራዝመው ያሉት ገደቦች ከመጠናቀቃቸው በፊት እንደምን ወደፊት መራመድ እንደሚቻል ተከታታይ ውይይቶች ይካሄዳሉ።

የንግድ ተቋማት ድጎማ

የቪክቶሪያ ንግድ ተቋማት በኮሮናቫይረስ ገደቦች ሳቢያ የተዳከመ ገቢያቸውን ለመደጎም በጥሬ ገንዘብና የታክስ እፎይታ የ$3 ቢሊየን ድጋፍ እንደሚደረግላቸውና ይህም በቪክቶሪያ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያውና ግዙፍ ድጎማ መሆኑን ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ አስታወቁ።

በኮሮናቫይረ በጣሙን ለተጎዱ አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ድርጅቶች $1.1 ቢሊየን የጥሬ ገንዘብ ድጎማ የሚያገኙ ሲሆን፤ እስከ $10 ሚሊየን የደመወዝ ክፍያ ለሚያወጡ በ2020-21 የፋይናንስ ዓመት ሙሉ በሙሉ ከደመወዝ ክፍያ ታክስ ነጻ ይሆናሉ።

ሌሎች አነስተኛ የንግድ ድርጅቶችም ለተለያዩ የዲጂታል ፕሮግራሞች ማከናወኛ $20 ሚሊየን እገዛ ይቸራቸዋል።

አሁን ባለው $1.5 ቢሊየን የታክስ እፎይታ ፕሮግራም በተጨማሪም $137 ሚሊየን የታክስ እፎይታ ይደረጋል። 

 


Share

3 min read

Published

By Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service