SKIP TO MAIN CONTENT

የአውስትራሊያ ሥራ አጥነት መጠን 4.0 ፐርሰንት ላይ ረግቷል

*** ከወንዶች ይልቅ የሴቶች የሥራ አጥነት ቁጥር ዝቅ ብሏል

News
Treasurer Josh Frydenberg. Source: Getty

1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Skip to article content

ምንም እንኳ በዐቃቤ ንዋይና ብሔራዊ ባንክ ዘንድ የአውስትራሊያ የወርኃ ማርች ሥራ አጥነት መጠን ወደ 3.7 ይወርዳል ተብሎ አመኔታ የነበረ ቦሆንም አራት ፐርሰንት ላይ ረግቷል።

ሆኖም ባለፈው ወር 17,900 ሥራ ፈላጊዎች ለሠራተኝነት በቅተዋል። 

የሥራ አጥነት ዳታ ዛሬ ይፋ ከመሆኑ በፊት በምጣኔ ሃብት ተጠባቢዎች ዘንድ ከ1974 ወዲህ ዝቅተኛ የሥራ አጥነት መጠን ወደሆነው 3.9 ፐርሰንት ይወርዳል የሚል ግምት አድሮ ነበር። 

በሌላ በኩል የአውስትራሊያ ስታቲስቲክስ ቢሮ ከወንዶች ይልቅ የሴቶች የሥራ አጥነት ቁጥር ዝቅ ማለቱን አስታውቋል። 

የቢሮው የሥራ ስታቲስቲክስ ዋና ኃላፊ ቢጆርን ጃርቪስ ከ1974 ወዲህ የሴቶች የሥራ አጥነት ቁጥር ከ3.8 ፐርሰንት ወደ 3.7 ፐርሰንት ዝቅ ያለ ሲሆን ከ2021 በመለስ የወንዶች የሥራ አጥነት መጠን ከ 4.2 ፐርሰንት ለውጥ አላሳየም። 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now