የአውስትራሊያ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር የቻይናና ታይዋን ውጥረት ከረገበ ዓለም 'የእፎይታ ትንፋሽ' እንደሚተነፍስ ገለጡ

ሕወሓት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለማድረጉን አስታወቀ

Acting Prime Minister Richard Marles.jpg

Acting Prime Minister Richard Marles hopes for a de-escalation in the Taiwan Strait. Credit: AAP / Jono Searle

የአውስትራሊያ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪችድ ማርልስ የቻይናና ታይዋን ውጥረት ከረገበ ዓለም "የእፎይታ ትንፋሽ' እንደምትተነፍስ ተናገሩ።

ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አውስትራሊያ በቻይናና ታይዋን ጉዳይ የምታካሂደው ውይይት ፕሮፌሽናል፣ ስክነትና ዲፕሎማሲን የተላበሰ እንደሚሆን ገልጠዋል።

በታይዋን ባሕረ ሰላጤ ዙሪያ ውጥረቶችን ያስፈነው የቻይና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ሲሆን፤ አስባቡም የዩናይትድ ስቴትስ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ነው።

የቻይናን ጦር ቦለስቲክ ሚሳይሎችን እስከማስወንጨፍ የደረሰው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ማብቃቱን የቻይና ምሥራቅ ዕዝ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

አቶ ማርልስ አውስትራሊያ ከቻይና ጋር የሰከነ ግንኙነትን ማድረግ እንደምትሻ ጠቁመዋል።

.

***

የሕወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ድርጅታቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር "ቀጥተኛ ግንኙነቶችን" አድርጓል ተብሎ መዘገቡን አስተባበሉ።

ቃል አቀባዩን ማስተባባያ ለመስጠት ግድ ያሰኘው AFP 'በትግራይ አማፅያንና በኢትዮጵያ መንግሥት" በኩል የቀጥታ ግንኙነት እንደተካሔደ የአፍሪካ ኅብረት መግለጫ ዋቤ አድርጎ መግለጡን ተከትሎ ነው።

አቶ ጌታቸው ሪፖርቱን በፍብረካነት ኮንነው 'ከቶውንም ያልሆነ' ሲሉ በቲዊተር ገፃቸው አሌ ብለውታል።


1 min read

Published

Updated

By NACA, Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now