ኢትዮጵያውያን አርበኞች ዳግም የጣሊያን ወረራን በ1941 / 1934 በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አመራር ድል የነሱበትና የእንግሊዝ ጦር በአጋርነት የተሳተፈበትን ድል በክብር ለመዘከር በጎንደርና ሎንዶን ከተሞች የመታሰቢያ ሐውልቶች ሊቆሙ ነው።
የመታሰቢያ ሐውልቶቹ በኢትዮጵያና እንግሊዝ ከተሞች ለማቆም መታቀዱን የገለጠው የኢትዮጵያ የዘውድ ምክር ቤት ሲሆን፤ በመጪው ዓመት የመጀመሪያው ሎንዶን ላይ የሚቆመው ሐውልት በክብር ተመርቆ ይፋ የሚሆነው በምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ልዑል ኤርሚያስ እንደሚሆንና አንድ ወይም ከዚያ በላይ የእንግሊዝ ከfተኛ ባለስልጣን በሥፍራው እንደሚገኙ ተመልክቷል።
ጎንደር ላይ የሚቆመው ሁለተኛው ሐውልትም በልዑል ኤርሚያስ ተመርቆ እንደሚከፈትና በሥፍራውም የኢትዮጵያ፣ እንግሊዝና የጋra ብልፅግና ከፍተኛ ባለስልጣናት እንደሚገኙ ተነግሯል።
በቅርቡም በአቀራረፁ ላይ ዳግማዊ ንግሥት ኤልሳቤጥ የተሳተፉበትና የኢትዮጵያውያን አርበኞችን፣ የእንግሊዝና የጋራ ብልፅግና ጦር አባላትን የሚዘክር "የጎንደር ድል" የክብር ሜዳል በዘውድ ምክር ቤቱ ተቀርፆ ለሽልማትነት በቅቷል።