SKIP TO MAIN CONTENT

ዩናይትድ ስቴትስ ቻይና ለሩስያ የምታደርገውን ድጋፍ አስመልክቶ ማስጠንቀቂያ ሰጠሁ አለች

*** የሩስያና የዩክሬይን ተኩስ አቁም ድርድር ለአራተኛ ጊዜ ያለ ስምምነት አበቃ፤ ሆኖም ዛሬ ይቀጥላል።

News
U.S. President Joe Biden participates in a virtual meeting with Chinese President Xi Jinping at the Roosevelt Room of the White House November 15, 2021. Source: Getty

1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Skip to article content

የፕሬዚደንት ጆ ባይደን ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ከአንድ ከፍተኛ የቻይና ባለስልጣን ጋር ሮም ላይ በተገናኙበት ወቅት ቻይና ለሩስያ የምታደርገውን ድጋፍ አስመልክተው ማሳሰቢያ መስጠታቸው ተነገረ። 

የባይደን አማካሪ ጆ ሱሊቫን ማሳሰቢያቸውን  ለገዲብ የቻይና የውጭ ጉዳይ አማካሪ ያንግ ጂቺ የተናገሩት ሮም ላይ በተገናኙበት ወቅት ነው።

የባይደን አስተዳደር ቻይና ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ለምታካሂደው ፉክክር የዩክሬይንን ጦርነት ለረጅም ጊዜ ብሔራዊ ጥቅሟ ማራመጃነት ልትጠቀምበት ትሻለች የሚል ስጋት አለው።   

የዩናይትድ ስቴትስ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ፤ አቶ ሱሊቫን የቤጂንግን አቋም ለማረጋገጥ ጥያቄ እንዳቀረቡና ለቻይና ሩስያ ላይ በምዕራባውያን የተጣሉትን ገደቦች ወደ ጎን የመግፋት እገዛን አስመልክቶ ያስጠነቀቁ መሆኑን አረጋግጠዋል።   

አያይዘውም፤ ዩናይትድ ስቴትስ አንድም አገር ሩስያ ለሚደርስባት ኪሳራ ማካካሻ እንዲያደርግ የማትፈቅድ መሆኑን በግልፅ ለቤጂንግ እንዳስታወቁና ያንንም ማድረግ መዘዞችን እንደሚያስከትል ለሁሉም አገራት በይፋ ማስታወቋን ተናግረዋል። 

ሩስያ ዩክሬይን

ከአስቸኳይ ተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ ለአራተኛ ዙር በሩስያና ዩክሬይን መካከል ለበርካታ ሰዓታት የተካሔደው ድርድር ያለ ስኬት አብቅቷል።   

ሆኖም አንድ የዩክሬይን ፕሬዚደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ተደራዳሪ እንዳሉት ድርድሩ "ቴክኒካዊ መገታት" የገጠመው ቢሆንም ዛሬ ማርች 15 እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now