ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚና ሺ ጂፒንግ ኢንዶዶኔዥያ እየተካሔደ ባለው የቡድን 20 ጉባኤ ላይ ተገናኝተው ተነጋገሩ

የአውስራሊያና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በመጪው ወርኅ ዲሴምበር 50ኛ ዓመቱን ያስቆጥራል።

ANTHONY ALBANESE G20 BALI

Australia’s Prime Minister Anthony Albanese meets China’s President Xi Jinping in a bilateral meeting during the 2022 G20 summit in Nusa Dua, Bali, Indonesia, Tuesday, November 15, 2022. (AAP Image/Mick Tsikas) Source: AAP / MICK TSIKAS/AAPIMAGE

የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትርና የቻይናው ፕሬዚደንት ሺ ጂንፒንግ ባሊ - ኢንዶኔዥያ እየተካሔደ ባለው የቡድን 20 ጉባኤ ላይ ተገናኝተው ተነጋገሩ።

ከ2016 ወዲህ በአውስትራሊያና ቻይና መሪዎች መካከል ይፋ የመሪዎች ግንኙነት ሲካሔድ ይህ የመጀመሪያው ነው።

ሁለቱ መሪዎች ተገናኝተው የተነጋገሩት ኑሳ ዱዋ ባሊ በሚገኘው ሙሊያ የቅንጦት ሪዞርት ውስጥ ነው።

Xi Albanese.jpg
Australia’s Prime Minister Anthony Albanese meets China’s President Xi Jinping in a bilateral meeting during the 2022 G20 summit in Nusa Dua, Bali, Indonesia, Tuesday, November 15, 2022. Credit: AAP Image/Mick Tsikas

ሁለቱ መሪዎች ገንቢ የሆነ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጠዋል።

ፕሬዚደንት ሺም በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት በቻይናና አውስትራሊያ መካከል የነበሩት ግንኙነት ሊያዩት በማይሹት መልኩ አዋኪ እንደነበር ጠቅሰው፤ ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስትር አልባኒዚ ደጋግመው ከቻይና ጋር አስተውሎት የተመላበት ግንኙነት ማድረግ እንደሚሹ መናገራቸውን እንደተረዱና በዚያ የተሳቡ መሆኑን ገልጠዋል።

የሁለቱ አገራት ግንኙነቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉና በሳቢያውም ቻይና በአውስትራሊያ ላይ ጥላ ያለችው የምጣኔ ሃብት ማዕቀብ ሊነሳ ይችላል የሚል ተስፋን አሳድሯል።

በ1972 የተጀመረው የአውስትራሊያና ቻይና ግንኙነት በመጪ ወርኅ ዲሴምበር 50ኛ ዓመቱን ያስቆጥራል።


1 min read

Published

By Kassahun Seboqa Negewo, NACA

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now