SKIP TO MAIN CONTENT

ሽምግልና ወደ ትግራይ

በነገው ዕለት 52 አባላት ያሉት የሀገር ሽማግሌዎች መማክርት ጉባኤ ልዑክ ወደ ትግራይ በመሔድ ከክልሉ መንግስትና ሌሎች የህዝብ ተወካዮች ጋር ይነጋገራል ተብሏል።

Amharic news 16 June, 2020
Source: Courtesy of PD

1 min read

Published

By Stringer


Skip to article content

የሀገር ሽማግሌዎቹ ወደ መቀለ የሚሔዱት በራሳቸው ተነሳሽነት ሲሆን የሀይማኖት መሪዎች፤ ታዋቂ ሰዎች፤ ምሁራን የተካተቱበት መሆኑን  አውሎ ሚዲያ ደርሶኛል ያለው መረጃ ያሳያል።

 እንደ መረጃው ከሆነ ሊቀ ጳጳስ  አቡነ ማትያስ ቀዳዊ  ፤ ብፁዕ ካርዲናል ብርሐነእየሱስ፤ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ፤ ፓስተር ፃዲቁ አብዶ፤ ፓስተር ታደሰ አዱኛ፤ ዶክተር ዮናስ ይገዙ ፤ ዶክተር እያሱ ኤሊያስ እንዲሁም  ከታዋቂ ሰዎች ደግሞ አትሌት ሺ አለቃ ሀይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ 52 ሰዎች ናቸው በፈቃዳቸው ወደ ትግራይ የሚሔዱት።

 የጉዞው ዋና አላማም ባለፉት ሁለት አመታት በትግራይ ክልል መንግስት እና በፌዴራል መንግስት መካከል እየተፈጠረ ያለው ልዩነት በህዝቦች አንድነት ላይ እየተፈጠረ ያለው መቃቃር ለማስቀረትና ለማጥበብ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ  ለመምከር ነው።

 ቡድኑ በትግራይ በሚኖረው ቆይታ ከክልሉ መሪዎች ፤ የሀገር ሽማግሌዎችና ተወካዮች ጋር  እርቅና መግባባት እንዲፈጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ነው የተባለው።

 በተለይም በፖለቲካ ሀይሎች መካከል ያለው አለመግባባት በህዝቦች ነባርና  የቆየ ግንኙነት ላይ እየፈጠረ ያለው ጫና እየሰፋ በመሆኑ የትግራይ ክልል መንግስትና የፌዴራል መንግስት ወደ መግባባት የሚመጡበትን መንገድ  ላይ በዋናነት ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now