የአውስትራሊያ ሥራ አጥነት ቁትር ለሶስት ተከታታይ ወራት 3.9 ፐርሰንት ላይ ረግቷል።
የሙሉ ቀን ሠራተኞች ቁጥር በ69 ሺህ 400 ከፍ ያለ ሲሆን፤ የግማሽ ቀን ሠራተኞች ቁጥር በ 8 ሺህ 700 ዝቅ ብሏል።
ወርሃዊ የሥራ ሰዓታት ወደ 17 ሚሊየን ወይም 0.9 ፐርሰንት ከፍ ብሏል።
የተቃዋሚ ቡድን የሠራተኞች ቃል አቀባይ ሴናተር ሚካኤላ ካሽ የአልባኒዚ መንግሥት ዝቅተኛ የሥራ አጥነት ቁጥርን ጠብቆ ሊቆይ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የሠራተኞች ጉዳይ ሚኒስትር ቶኒ በርክ በበኩላቸው ጊዜው የአውስትራሊያ ሥራ አጥነት ቁጥር ዝቅ ማለትን ተከትሎ የደመወዝ ጭማሪ ሊሆን እንደሚገባ አመላክተዋል።
የቤተሰብና የቤት ውስጥ ጥቃት
የፍትሕ ሥራ ኮሚሽን መንግሥት የቤተሰብና የቤት ውስጥ ጥቃት ሰለባዎች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እንዲሆናቸው ብሔራዊ የሠራተኞች ክፍያ ደረጃዎችን የጠበቀ የ10 ቀናት ክፍያ እንዲያገኙ የሚቀርብለትን ረቂቅ ተመልክቶ ከውሳኔ ላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህንኑ አስመልክቶ ኮሚሽኑ ማብራሪያ የጠየቀ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ትስስሮሽ ያላቸው ድርጅቶች የጋራ ብልፅግ ናው መንግሥት ያቀረበውን የ10 ቀናት ክፍያ ረቂቅ ተመልክተው ምላሻቸውን እስከ ጁላይ 1 ባሉት ጊዜያት ውስጥ እንዲያቀርቡ ጥሪ ቀርቧል።

