የምዕራብ አውስትራሊያ ፖሊስ ከእንግሊዝ፣ አየርላንድና ኒውዝላንድ የፖሊስ ሠራዊት አባላትን ሊመለምል ነው

የጎርፍ አደጋ አሳሳቢ በሆነባቸው የቪክቶሪያና ኒው ሳውዝ ዌይልስ አካባቢ ነዋሪዎች ቀዬዎቻቸውን ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዞች ተላለፉ

Police officers in the UK, Ireland and New Zealand are being invited to take up roles in Western Australia.jpg

Police officers in the UK, Ireland and New Zealand are being invited to take up roles in Western Australia. Credit: AAP / RICHARD WAINWRIGHT

የምዕራብ አውስትራሊያ ፖሊስ ለአውስትራሊያ ዜግነት የሚያበቃ ዓለም አቀፍ የፖሊስ ሠራዊት አባላት ምልመላ ዘመቻ ጀመረ።

ምልመላው አተኩሮ ያለው ከአውስትራሊያ ጋር ተመሳሳይ የፖሊስ አሠራር ካላቸው አገራት እንግሊዝ፣ አየርላንድና ኒውዝላንድ ላይ ነው።  

ከመመዘኛዎቹም ውስጥ የሶስት ዓመታት የፖሊስ ሥራ ልምድና ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በታች ሊሆን እንደሚገባ የምዕራብ አውስትራሊያ ፖሊስ ኮሚሽነር ገልጠዋል።

የምዕራብ አውስትራሊያ ፖሊስ ሚኒስትር ፖል ፓፓሊያ የባሕር ማዶው ምልመላ በመላው አውስትራሊያ የሚካሔደው ምልመላ አንዱ አካል እንደሆነ አመልክተዋል።

የማክጋዋን መንግሥት ከ1,000 በላይ የፖሊስ ሠራዊት ለመቅጠር አልሟል። 


የጎርፍ ማስጠንቀቂያ

በምሥራቃዊ ክፍለ አገራት በተለይም ቪክቶሪያ እና ኒው ሳውዝ ዌይልስ ላይ የጎርፍ ማስጠንቀቂያው ፀንቶ አለ።

የቪክቶሪያ ጉልበርን ወንዝ፣ የማዕከላዊ ሰሜን ቪክቶሪያ ሼፐርተን፣ ሲሞርና ማርቺሰን ከፍተኛ የጎርፍ ማስጠንቀቂያ ተሰTቶባቸዋል።

ለበርካታ ነዋሪዎች ቀዬአቸውን ለቅቀው ለመውጣት በእጅጉ የዘገዩ መሆኑ የተመለከተ ሲሆን፤ የቪክቶሪያ ፖሊስ ረዳት ኮሚሽነር ዴቪድ ክሌይተን ነዋሪዎች ማስጠንቀቂያዎችን ግብር ላይ ማዋሉ በእጅጉ ጠቃሚ እንደሆነ አሳስበዋል።

 ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ በደቡብ ሪቬሪና ሪጂን ናሬንዴራ እና በማዕከላዊ ምዕራብ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ፎርብስ ቀዬዎቻቸውን ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዞች ተላልፈዋል።  



 



 



Share

Published

By Kassahun Seboqa Negewo, NACA
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service