ዓለም አቀፍ የመንገደኞች መርከቦች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነሳ

*** ክሩዝ መርከቦቹ ከዛሬ እሑድ ኤፕሪል 17 ጀምሮ ወደ አውስትራሊያ መቅዘፍ ይችላሉ።

News

The Spectrum of the Seas cruise ship, sits in Sydney Harbour in Sydney, Australia, on Wednesday, March 18, 2020. Source: Getty

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ የአውስትራሊያ ዓለም አቀፍ ድንበር በመዘጋቱ እገዳ ተጥሎበት የነበረው የክሩዝ መርከብ ጉዞ ዳግም ፈቃድ በማግኘቱ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ደስታውን ገለጠ።

መንገደኞችን የጫኑ መርከቦች የጥንቃቄ ደንቦችን ግብር ላይ በማዋል ከዛሬ እሑድ ኤፕሪል 17 ጀምሮ ወደ አውስትራሊያ መቅዘፍ ይችላሉ።

በጤና ጥንቃቄዎቹ መሠረትም ተሳፋሪዎች የፊት ጭምብሎችን ማጥለቅ፣ የኮቪድ-19 ምርመራዎችን ማድረግና ሙሉ ክትባቶችን መከተብ ይጠበቅባቸዋል።    

የመጀመሪያዋ ደራሽ መርከብ Pacific Explorer ስትሆን፤ ነገ የሰኞ ፋሲካ ዕለት ሲድኒ ትደርሳለች። 

የቱሪዝም ኒው ሳውዝ ዌይልስ ተጠሪ ግሬግ ቢኒስኪን የመንገደኞች መርከቦቹ ዳግም ወደ አውስትራሊያ መመለስ ለቱሪዝም ኦፕሬተሮች በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ለSBS ገልጠዋል።  

 


1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now