ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን መንግሥታቸው ዳግም ከተመረጠ ሴናተር አን ራስተን የጤና ሚኒስትር እንደሚሆኑ አስታወቁ

*** የሌበር መሪ አንቶኒ አልባኒዚ የአን ራስተን ሚኒስትራዊ ስየማ የሞሪሰን መንግሥት ዳግም ከተመረጠ የሜዲኬይር በጀት ቅነሳ አመላካች ነው ሲሉ አሳሰቡ

News

Anne Ruston will replace Greg Hunt as federal health minister, Scott Morrison has confirmed. Source: AAP

የፌዴራል መንግሥቱ ሜይ 21 በሚካሔደው ምርጫ በለስ ቀንቶት ዳግም ከተመረጠ አን ራስተን የጤናና የአረጋውያን ክብካቤ ሚኒስትር እንደሚሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ዛሬ እሑድ ኤፕሪል 17 አስታወቁ። 

ሴናተር ራስተን በአሁኑ ወቅት የማኅበራዊ አገልግሎቶች ሚኒስትር ሲሆኑ፤ ተተኪነታቸው ከፖለቲካው ዓለም በሚገለሉት ግሬግ ሃንት ፈንታ ነው። 

 

አቶ ሞሪሰንና አቶ ሃንት በዛሬው ዕለት ለዓይነት አንድ ስኳር በሽታ ግሉኮስ መቆጣጠሪያ ፕሮግራም ማስፋፊያ የሚውል በሊብራል/ናሽናልስ ፓርቲ በኩል መመደቡን ይፋ አድርገዋል። 

የሴናተር ራስተንን የጤና ሚኒስትርነት ስየማ ተከትሎ የሌበር ፓርቲ መሪ አንቶኒ አልባኒዚ፤ ስየማው የሚያመልክተው የሞሪሰን መንግሥት ዳግም ከተመረጠ የሜዲኬር በጀተ ቅነሳ እንደሚገጥመው ማመላከቻ ነው በማለት ትችትና ማሳስቢያ ሰንዘረዋል። 

ለአቶ አልባኒዚ ትችት ሰበቡ፤ ወ/ሮ ራስተን በ2015 'ሜዲኬርን አሁን ባለበት ሁኔታ ደጉሞ መዝለቅ አዋኪ ነው' ሲሉ በሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ቤት ንግግር ከማድረጋቸው ጋር የተያያዘ ነው።  

ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ የአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን አሳሳች የፖስታ ድምፅ መስጫ ማመልከቻ ቅፅን አስመልክቶ ለፖለቲካ ፓርቲዎች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ልኳል። 

ኮሚሽኑ አሳሳች ቅፆች ለመራጮች የመላካቸውን ሪፖርት ነቅሶ፤ የኮሚሽኑን ሐምራዊ ቀለም የተላበሱ ቅፆች መላካቸውን ጠቅሷል። 

ድርጊቱ አሳሳች ብቻም ሳይሆን ሕገ ወጥ መሆኑንም አሳስቦ አስጠንቅቋል።   


1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now