ኢንዶኔዥያ የተካሔደው የቡድን - 20 የፋይናንስ ሚኒስትሮች ስብሰባ የዩክሬይን ጦርነትን አስመልክቶ የጋራ አቋም ሳይዝ አከተመ

*** የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ መስፋፋትን ተከትሎ የፊት ጭምብል የማጥለቅ ድንጋጌ ግብር ላይ እንዲውል ጥሪዎች እየቀረቡ ነው

News

Indonesian Finance Minister Sri Mulyani (2n L) delivers her speech during the G20 Finance Ministers Meeting in Nusa Dua, on July 15, 2022. Source: Getty

ከጁላይ 15 - 16 ለሁለት ቀናት ባሊ - ኢንዶኔዥያ የተካሔደው የቡድን - 20 የፋይናንስ ሚኒስትሮች ስብሰባ የዩክሬን ጦርነትን አስመልክቶ በታዳሚ አገራት የአቋም መለያየት ሳቢያ የጋራ አቋም መግለጫው ውስጥ ሳያካትት አክትሟል። 

የዩናይትድ ስቴትስ በጅሮንድ ጃኔት የለን የጋራ መግለጫው ላይ የዩክሬይን ጦርነትን አስመልክቶ አንድ ዓይነት አቋም መያዝ ያልተቻለው የተላያዩ አገራት ተመሳሳይ ዕይታዎችን ባለማንፀባረቃቸው እንደሆነ ገልጠዋል። 

ሆኖም በስብሰባው መዝጊያ ላይ የወቅቱ የቡድን - 20 ሰብሳቢ የሆነችው ኢንዶኔዥያ ፋይናንስ ሚኒስትር ስሪ ሙሊያኒ ምጣኔ ሃብት ላይ ባተኮረውና በሉላዊ ጉዳዮች "ጠንካራ ሉላዊ መግባባት" እንደሚያሻ ባመላከተው የፋይናንስ ሚኒስትሮችና የማዕከላዊ ባንክ ገዢዎች መግለጫ ላይ በታካይነት የዩክሬይን ጦርነትን አስመልክቶ የተነሱ የተለያዩ አተያዮች እንዲንፀባረቁ አድርገዋል።    

በሚኒስትሮቹ ስብሰባ ወቅት ምዕራባውያን አገራት በሩስያ ላይ ጠንካራ ማዕቀቦችን መጣልንና ሩስያን በዩክሬይን ጦርነት በጦር ወንጀሎች ተጠያቂ መሆንን ሲያነሱ፤ ቻይና፣ ሕንድና ደቡብ አፍሪካ አቋማቸውን በዝምታ ምላሽ አንፀባርቀዋል። 
News
US Secretary of Treasury Janet Yelle. Source: Getty
በጅሮንድ የለን በቡድን - 20 ሚኒስትሮች ዘንድ ያሉ ልዩነቶች እንዳሉ ሆነው እየከፋ በመሔድ ላይ ያለውን የምግብ ዋስትና ቀውስ ለመግታት የጋራ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አመላክተዋል።  

በስብሰባው ላይ የዩክሬይን ተወካይ በተጋባዥነት ተገኝተዋል። 

ቀጣዩ የቡድን - 20 አራተኛው ዙር ስብሰባ ኦክቶበር 2022 ዋሽንግተን ዲሲ - ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ይካሔዳል። 

የፊት ጭምብል

የክፍለ አገራት መሪዎች አውስትራሊያውያን የኮቪድ - 19 መስፋፋትን ለመገደብ የፊት ጭምብሎችን እንዲያጠልቁ የማሳሳቢያ ጥሪዎችን እያቀረቡ ነው።

ለማሳሳቢያ ጥሪዎቹ አስባብ የሆነውም በትናንትናው ዕለት የታደመው ብሔራዊ ካቢኔ የፊት ጭምብል ማጥለቅን ግዴታ የሚያደርገውን ድንጋጌ ግብር ላይ ለማዋል ከይሁንታ ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻሉ ነው። 

በተወሰኑ ክፍለ አገራት ክረምቱ ለኮሮናቫይረስ መስፋፋት አስተዋፅዖ ስለሚኖረው ያለ መከላከያ እርምጃዎች የኮሮናቫይረስ ተዛማችነት ከሚገመተው በላይ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋትን አሳድሯል። 

የደቡብ አውስትራሊያ ተጠባባቂ ፕሪሚየር ሱዛን ክሎዝ በኮቪድ - 19 ተጠቅተው ሆስፒታል የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከጁላይ ወር መጨረሻ ላይ ሊያሻቅብ ይችላል የሚል ስጋት በመንግሥት ዘንድ ያደረ መሆኑን ገልጠዋል።
News
Victorian Health authorities are recommending residents resume wearing face masks indoors as COVID-19 infections begin to rise again across Australia. Source: Getty
የፊት ጭምብሎችን የማጥለቅ ጥሪ በጤና ባለሙያዎች ዘንድ ድጋፎችን አግኝቷል። 

የአውስትራሊያ የሕክምና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዚደንት ዶ/ር ኦማር ኮሺድ አዲስ የኮሮናቫይረስ ማዕበል አገሪቱን በመታበት ወቅት የፊት ጭምብል ድንጋጌን ግብር ላይ ማዋል አስፈላጊ እንደሆነ አፅንዖት ሰጥተው አሳስበዋል።

 

 


Share

Published

By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service