“ከሕወሓት ጋር በድብቅ የሚደረግ ውይይት አንቀበልም” - ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል

የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች መማክርት በመቐለ

Amharic news 17 June, 2020

Source: Supplied

በትናንትናው ዕለት የኢትዮጵያ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች መማክርት በኢትዮጵያ በተፈጠረው ፖለቲካዊ ውጥረት ዙሪያ በመቐለ ከተማ ተገኝተው ከትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ጋር የውይይት መደረክ አካሂደዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ፣ የትኛውንም ዓይነት ልዩነት በውይይት ለመፍታት ፣ የትግራይ ክልል አመራሮች ከፌዴራል መንግስት አመራሮች ጋር በክብ ጠረጴዛ በመነጋገር አጠቃላይ ሀገራዊ መግባባት ላይ እንዲደርሱ መጠየቃቸውን ህወሓት አስታውቋል፡፡

 አል አይን እንደዘገበው ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት የትግራይ ክልል ም/ ርእስ መስተዳድር  ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) “ውይይቱ በመጨረሻ ሰዓት የተጀመረ ቢሆንም መሞከሩ ግን ጥሩ ነው” ያሉ ሲሆን  “የውውይት መድረክ መፈጠር ካለበት፣ ሁሉም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችን የሚወክሉ ፌደራሊስት ሀይሎች የሚሳተፉበት አገራዊ መድረክ መዘጋጀት አለበት እንጂ ከህወሓት/ከትግራይ መንግስት ጋር በድብቅ የሚደረግ ውይይት አንቀበልም፤ ትርጉምም አያመጣም” ማለታቸውን ድርጅታቸው ገልጿል፡፡

 “ብልጽግና ፓርቲ ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ በሀገሪቱ አምባገነናዊ ሥርዓት ለመገንባት እየተሯሯጠ ነው” በሚል ቡድን ብለው የሰየሙትን ብልጽግናን የተቹት ዶ/ር ደብረፅዮን “ባለፉት 2 ዓመታት የትግራይ ህዝብና መንግስት በአገሩ እንደ ባእድ ተቆጥሮ የተለያዩ በደሎች ሲደርሱበት ዝም ብላችሁ ተመልክታችኋል” በማለት የሃይማኖት አባቶችን እና የሀገር ሽማግሌዎችንም ወቅሰዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎችቹ የመቀሌ ቆይታቸውን ዉጤት በመያዝ ከፌደራሉ መንግስት ጋርም ዉይይት ያደርጋሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡


1 min read

Published

By Stringer


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now