ኢትዮጵያና ሩሲያ በወታደራዊ ቴክኒክ መስክ ተባብረው ለመሥራት ጁላይ 12, 2021 ስምምነታቸውን በፊርማ አፀደቁ።
በሁለቱ አገራት መካከል የተካሔደውን የስምምነት ፊርማ በኢትዮጵያ በኩል ያኖሩት የመከላከያ ሚኒስቴር ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ማርታ ሊዊጅ ናቸው።
ከስምምነቱ ላይ የተደርሰውም በኢትዮጵያና ሩስያ ተወካዮች ሶስት ቀናት ይየፈጀው የጋራ ውይይት እንዳበቃ ነው።
የወታደራዊ ቴክኒክ ስምምነቱ "የሠራዊትቱን አቅም በዕውቀት፣ በክህሎትና ቴክኖሎጂ ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት ፋይዳው የጎላ" መሆኑን ሚኒስትር ደኤታዋ ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች ገልጠዋል።
ማዕቀብ የአውሮፓ ኅብረት
የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳዮች ዋና የፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ መጣል እንዲቻል ለኅብረቱ አገራት አሳሰቡ።
አቶ ቦሬል ትግራይ ውስጥ ያለው ሁኔታ እየከፋ ያለ መሆኑን ጠቅሰው ሁኔታዎች አሳማኝ ሆነው ሲገኙ የማዕቀብ እርምጃዎችን ለመውሰድ የኅብረቱ አገራት ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል።
አክለውም "ምንም እንኳ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተኩስ ማቆም ዕወጃ ቢደረግም፤ ትግራይ ውስጥ እያየን ያለነው፤ ስጋት አድሮብን ያለው ትግራይ ብርቱ ሰብዓዊ ቀውስ እንደሚገጥማት ነው" ብለዋል።

European Union foreign policy chief Josep Borrell. Source: Getty
ቦሬል ይህን የተናገሩት ጁላይ 12 ብራስልስ ውስጥ የተካሔደው የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳዮች ምክር ቤት ስብሰባ አብቅቶ በጋራ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት ጁን 28 የተናጠል ተኩስ ማቆም ዕወጃ ማድረጉና መቀሌን ለቅቆ መውጣቱ ይታወሳል።
Share

