ዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ ትናንት ቅዳሜ ኤፕሪል 9 ሕይወታቸው ያለፈውን ባለቤታቸውን ልዑል ፊሊፕን በቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ላይ ተገኝተው ተሰናበቱ።
በኮሮናቫይረስ መስፋፋት ሳቢያ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት 30 ለቀስተኞች ብቻ ሲሆኑ፤ ዊንድሶር ቤተመንግሥት ውስጥ በሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተካሄደው የለቅሶው ሥነ ሥርዓት ለ50 ደቂቃዎች ተካሂዷል።
የ94 ዓመቷ ንግሥት ከባለቤታቸው ሕልፈተ ሕይወት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ጥቁር የኃዘን ልብስና ጥቁር ይርፊት ጭምብል አጥልቀው ታይተዋል።

የቅርብ የቤተሰብ አባላትም በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ ታድመዋል።

የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን
ከ600 ሺህ በላይ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ሃብትና ንብረታቸው ማስመዝገባቸውን የፌዴራል የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የሃብት ምዝገባ መከናወኑን የፌዴራል የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ወዶ አጦ ገልጠዋል።
ኮሚሽኑ በዕቅድ ከያዘው 95 በመቶውን ማሳካት እንደቻለ መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

