የማኅበራዊ ሚዲያ ግዙፍ አካል ፌስቡክ አውስትራሊያ ውስጥ ያሉ አታሚዎችና የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ዜናዎችን ማጋራትና መመልከት እንዳይችሉ አግዷል።
ይህን እርምጃ የወሰደውም የፌዴራል መንግሥቱ ፌስቡክ ለሚዲያ ተቋማት ዜናዎችና ሌሎች አቅርቦቶች ክፍያ እንዲፈጽም ግድ የሚያሰኝ ድንጋጌ በመንደፉ የተቃውሞ አጸፋ ነው።
የአውስትርሊያና ኒውዝላንድ ፌስቡክ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዊሊያም ኢስተን ይህንኑ አስመልክተው ሲናገሩ ፤
"በረቂቅነት የቀረበው ድንጋጌ በእኛ የግልጋሎት መድረክና ዜናዎችን በሚያቀርቡቱ አታሚዎች ዘንድ ያለው ግንኙነት ላይ መሠረታዊ የሆነ የተዛበ ዕሳቤ አለ። ይህም ከማያወላዳ ምርጫ ላይ እንድደርስ ግድ ብሎናል፤ የግንኙነቱን ዕውነታዎች አሌ የሚለውን ሕግ ተቀብሎ መፈጸም ወይም የዜናዎች አቅርቦት ግልጋሎታችንን አውስትራሊያ ውስጥ ማቆም። ከታላቅ ሐዘን ጋር የመጨረሻውን መርጠናል" ብለዋል።
ይህም ማለት፤
- የኣውስትራሊያና ዓለም አቀፍ ፌስቡክ ተጠቃሚዎች የአውስትራሊያን ዜናዎች መመልከትና ማጋራት ወይም የዓለም አቀፍ ዜናዎችን ማጋራት አይቻላቸውምለአውስትራሊያ የሚዲያ ተቋማት፤
- ምንም ኣይነት የዜና አቅርቦቶችን ማሰራጨት ወይም ማጋራት አይቻላቸውም
- አስተዳደራቸው ከፌስቡክ ገፃቸው ሌሎች ግልግሎትችን መጠቀም ይችላል
- ፌስቡክ ዳታን አካትቶ ሌሎች ግልጋሎቶችን መስጠቱን ይቀጥላል
ፌስቡክ ረቂቅ ህጉን ተከትሎ እኒህን እርምጃዎች ቢወስድም በፌዴራል መንግሥቱ በኩል ግና በአቋሙ ጸንቶ እንደሚቀጥል የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ፖል ፍሌቸር አስታውቀዋል።

