"ከሕግ ውጪ የሚካሔዱ አፈናዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ እንጠይቃለን" እናት ፓርቲ

*** እናት ፓርቲ በብልፅግና ፓርቲ ለሚመራው አስተዳደር "ሥርዓቱ ከመወደድ ይልቅ መጠላትን፣ ከሕጋዊ አካሔድ ይልቅ አፈናን፣ ከመከበር ይልቅ መፈራትን ከመረጠ በሚያስገርም ፍጥነት ከሕዝብ እየተነጠለ፣ ውድቀቱንም እያፋጠነ፣ ወዲህም የሰውን ልጅ ሕይወት እየቀጠፈ መቀጠሉ አይቀሬ ለመሆኑ ነጋሪ አያሻም" ሲል አሳስቧል።

News

The gilt bronze sculptor of Lady Justice. Source: Getty

የእናት ፓርቲ ዛሬ ግንቦት 11 "አፈና ለደርግና ለሕወሓት ምን ጠቀመ?" ሲል ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሔዱ ያሉ አፈናዎች እንዲገቱና ታፍነው ያሉ ዜጎች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ አሳሰበ። 

ፓርቲው በብልፅግና ፓርቲ ለሚመራው አስተዳደር ማሳሳቢያውን ሲያጠናክርም "ሥርዓቱ ከመወደድ ይልቅ መጠላትን፣ ከሕጋዊ አካሔድ ይልቅ አፈናን፣ ከመከበር ይልቅ መፈራትን ከመረጠ በሚያስገርም ፍጥነት ከሕዝብ እየተነጠለ፣ ውድቀቱንም እያፋጠነ፣ ወዲህም የሰውን ልጅ ሕይወት እየቀጠፈ መቀጠሉ አይቀሬ ለመሆኑ ነጋሪ አያሻም" ብሏል።  

አያይዞም ሕጋዊ እርምጃዎች ግብር ላይ እንዲውሉ ባለ ሶስት ነጥብ መጠይቆችን ሲያቀርብ፤

  • ባለፉት 50 ዓመታት ተሞክሮ የከሰረን ተመሳሳይ ሥርዓት ለመድገም መሞከር ሕዝብን ወደ ተለመደው የአመፅ መንገድ የሚመራ ተግባር ስለሆነ ከሕግ አግባብ ውጪ የሚካሔዱ አፈናዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ እንጠይቃለን። 
  • የታፈኑ ዜጎች ማን በምን አግባብ እያፈናቸው እንደሆነ ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግና በወንጀል የተጠረጠሩ ከሆነም በሕግ አግባብ በአስቸኳይ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ይህ ሊሆን ካልቻለ እንዲለቀቁ እንጠይቃለን። 
  • ቢያንስ ይችኑ የቀጨጨች የፍርድ ሥርዓት ይባስ ብሎ የሚሰብር አካሔድ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጪ ሰዎችን የሚያፍኑና የሚጠልፉ ቡድኖች ወደ ሕግ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን

ብሏል።

 

  

 


1 min read

Published

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now