ምንም እንኳ ወርኃ ኤፕሪል 4,000 ብቻ አዲስ የሥራ ዕድሎች የተመዘገበበት ቢሆንም የአውስትራሊያ ሥራ አጥነት ቁጥርን ከ 4 ፐርሰንት ወደ 3.9 ፐርሰንት ዝቅ ማስደረግ ችሏል።
ከ1978 ወዲህ የአውስትራሊያ ሥራ አጥነት ቁጥር ወርሃዊ ዳታ ከ4 ፐርሰንት በታች ሲሆን ይህ የመጀመሪያ ጊዜው ነው።
ዳታውን ይፋ ያደረገው የስታቲስቲክስ ቢሮ የሥራ ተሣትፎ 66.3 ፐርሰንት ማመልከቱን ጠቁሟል።
ፖሊን ሃንሰን
የዋን ኔሽን ፓርቲ መሥራችና መሪ ፖሊን ሃንሰን በኮቪድ-19 ተያዙ።
የኮቪድ-19 ክትባት ያልተከተቡት ሃንሰን በቫይረሱ መጠቃታቸውን ዛሬ ለ KIIS-FM ራዲዮ ጣቢያ ጋር ቃለ ምልልስ ባካሔዱት ወቅት ገልጠዋል።
ሃንሰን በቫይረሱ በመያዛቸው ሳቢያም ለሰባት ቀናት ወሸባ ስለሚገቡ የቅዳሜውን አገር አቀፍ ምርጫ ጨምሮ በምርጫ ዘመቻ ላይ አይሳተፉም።
የታዝማኒያው የግል የምክር ቤት ተወዳዳሪ አንድሩ ዊልኪም እንዲሁ በኮቪድ-19 በመጠቃታቸው ከምርጫ ዘመቻ ተገልለዋል።

