የቪክቶሪያ ዕለታዊ ኮሮናቫይረስ ቁጥር ወደ 21 ዝቅ አለ

*** ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓታት 602 ሰዎች በኮቨድ-19 ተይዘዋል

Dan

Victorian Premier Daniel Andrews looks on during a press conference in Melbourne. Source: AAP

በዛሬው ዕለት 21 ሰዎች ቪክቶሪያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ ሲጠቁ ሰባት ሕይወታቸውን አጥተዋል።

ሕይወታቸው ያለፈውን ሰባት ሰዎች ጨምሮ በመላው ቪክቶሪያ 757 በአገር አቀፍ ደረጃ 844 ሰዎች በቫይረሱ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

የሜልበርን 14 ቀናት አማካይ ዕለታዊ የኮሮናቫይረስ ቁጥር 39.3 ደርሷል።

በቪክቶሪያ መንግሥት በኩል የተጣሉ የኮቨድ - 19 ገደቦችን ለማላላት የሚሻው የ14 ቀናት አማካይ የቫይረስ ተዛማችነት ቁጥር እስከ 50 የሚደርስ ነው።    

ኮቨድ - 19 - ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 602 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲጠቁ 12 ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በጠቅላላው ኢትዮጵያ ውስጥ 67 ሺህ 515 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ 27 ሺህ 638 አገግመዋል፤ 38 ሺህ 803 በአሁኑ ወቅት በቫይረሱ ተጠቅተው ይገኛሉ።

በኮሮናቫይረስ ሳቢያ እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ 1 ሺህ 72 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ - ጠቅላይ ፍርድ ቤት 

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩት ዝነኛዋ ሩዝ ባደር ጊንስበርግ በ87 ዓመታቸው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ዳኛ ጊንስበርግ በካንሰር በሽታ ለረጅም ጊዜ ታመው የነበሩ ሲሆን በአያሌ አሜሪካውያን በተለይም በሴቶች ዘንድ የዕውቀት፣ ፍትሕና የጾታ እኩልነት ተምሳሌት ሆነው ይታዩ የነበሩና የሚታሰቡ ናቸው።
Ruth
A marcher holds a sign that says "Ruth Shall Set Us Free" during the Woman's March in NY in January 2020. Source: Getty Images
የዳኛ ጊንስበርግ ተተኪ አስመልክቶ የ2020 ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ላይ ብርቱ ፖለቲካዊ ትንቅንቅ እንደሚፈጥር ይጠበቃል።


Share

1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service