የአውስትራሊያ አሽከርካሪዎች የዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥን ብሔራዊ የሐዘን ቀን ተከትሎ የእጥፍ ነጥቦች መቀጮ ሊያገኛቸው ነው።
የእጥፍ ነጥቦች መቀጮዎቹ ግብር ላይ የሚውሉት ከ12:01am ሐሙስ ሴፕቴበር 21 / መስከረም 12 እስከ 11:59pm ሴፕቴበር 25 መስከረም 15 ይሆናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ ለንግሥት ኤልሳቤጥ ሕልፈተ ሕይወት መዘከሪያ ሐሙስ ሴፕቴምበር 21 / መስከረም 12 ብሔራዊ የሐዘን ቀን ሆኖ እንዲውል መንግሥታቸው መወሰኑን አስታውቀዋል።
የእጥፍ ነጥቦች መቀጮ ቀናት፤
- በኒው ሳውዝ ዌይልስና የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ከረቡዕ እስከ እሑድ
- በምዕራብ አውስትራሊያ ከዓርብ እስከ ሰኞ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
- ኩዊንስላንድ ለሁለተኛ ጊዜ በ12 ወራት ውስጥ ጥፋት ላይ የተገኙ አሽከርካሪዎች የእጥፍ ነጥቦች መቀጮ ይገጥማቸዋል።
- ቪክቶሪያ፣ ታዝማኒያ፣ ደቡብ አውስትራሊያና ኖርዘን ቴሪቶሪ የእጥፍ ነጥቦች መቀጮ የላቸው።
የኒው ሳውዝ ዌይልስ የእጥፍ ነጥቦች መቀጮ፤
ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ 10 ኪ/ሜትርና ከዚያ ዝቅ ያለ (2 ነጥቦች)
ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ 10 ኪ/ሜትርና ከዚያ ከፍ ያለ (6 ነጥቦች)
ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ ከ20 ኪ/ሜትር በላይ (8 ነጥቦች)
ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ ከ30 ኪ/ሜትር በላይ (10 ነጥቦች)
ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ ከ45 ኪ/ሜትር በላይ (12 ነጥቦች)
የራሳቸውን የመቀመጫ ቀበቶ ያልታጠቁ አሽከርካሪዎች (6 ነጥቦች)
ተሳፋሪዎቻቸው ቀበቶ ሳይታጠቁ ለሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች (6 ነጥቦች)
የራስ ሔልሜት ሳያጠልቁ ሞተርሳይክል የሚያሽከረክሩ ነጂዎች (6 ነጥቦች)
ተሳፋሪያቸው ሔልሜት ሳያጠልቅ ሞትርሳይክል ለሚነዱ (6 ነጥቦች)
እያሽከረከሩ ሞባይል ስልክ የሚጠቀሙ (8 ነጥቦች)
ሆስፒታል
የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ ለዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ መታሰቢያ እንዲሆን የማሩንዳህ ሆስፒታልን በንግሥቲቱ ስም በመቀየራቸው ትችት ተሰንዝሮባቸዋል።
የነባር ዜጎች ቋንቋን የያዘን ሆስፒታል ስም በንግሥቲቱ ስም መሰየም ተገቢ አይደለም ሲሉ ትችቱን የሰነዘሩት የነባር ዜጎች ቡድናትና መሪዎች ናቸው።
ሆኖም፤ ፕሪሚየር አንድሩስ ሆስፒታሉ የሚገነባበት አካባቢ በጠቅላላው የሚጠራው በማሩንዳህ በመሆኑ ለጤና ሥርዓትና ጤና ክብካቤ ታላቅ ደጋፊ በነበሩት ንግሥት ስም ለመታሰቢያቸው መሰየሙ ተገቢ ነው ከማለት አላመነቱም።
በአንድ ቢሊየን ዶላርስ የሚገነባው ሆስፒታል አዲስ በመሆኑ አዲስ ስም ያስፈልገዋልም ብለዋል።