አውስትራሊያ ለገቡ የዩክሬን ስደተኞች ለሶስት ዓመታት የሥራ፣ የትምህርትና የሜዲኬይር ግልጋሎቶች ተጠቃሚ የሚያደርግ ቪዛ ተፈቀደ

*** የዩክሬይን ፕሬዚደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ በድጋሚ "ትርጉም ያለው" የሰላም ንግግር ለማድረግ ለሩስያ ጥሪ አቀረቡ።

News

(L-R) Iryna Balvan, Nastya Balvan, Chrestyna Kmetj and her daughter are pictured at Melbourne airport. Source: SBS

የፌዴራል መንግሥቱ አውስትራሊያ ለገቡ ዩክሬናውያን ጊዜያዊ የሰብዓዊ ቪዛ ሊሰጥ ነው።

ቪዛው አውስትራሊያ የገቡ ዩክሬናውያንን ለሶስት ዓመታት የሥራ፣ የትምህርትና የሜዲኬር ግልጋሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል።

አውስትርሊያ ከ3,000 በላይ ለዩክሬይን ስደተኞች የሰብዓዊ ቪዛ ሰጥታለች። 

መንግሥት ተጨማሪ ወታደራዊ እርዳታ ማድረጉንም አስታውቋል። 

የሰላም ንግግር

የዩክሬይን ፕሬዚደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ በድጋሚ "ትርጉም ያለው" የሰላም ንግግር ለማድረግ ለሩስያ ጥሪ አቀረቡ።

ሁለቱ አገራት ባለፉት ሳምንታት ከስምምነት ላይ ያላደረሱ ተከታታይ ድርድሮችን በልዑካኖቻቸው በኩል አድርገዋል። 

የሩስያና ዩክሬይን ጦርነት የቀጠለ ሲሆን በዩክሬይን ማሪዩፖል ከተማ ላይ ከፍተኛ ጥቃት እየደረሰ ነው። 

ፕሬዚደንት ዜሌንስኪ ዩክሬይንን ከሩስያ ወረራ እየተከላከሉ ላሉ ወታደሮች ማበረታቻ የሜዳል ሽልማቶችን ከምስጋና ጋር ሰጥተዋል።

በሌላም በኩል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በጦርነቱ ሳቢያ የ800 ሰላማዊ ሰዎች ሕይወት መቀጠፉንና 3.3 ሚሊየን ዩክሬናውያን ለስደት መዳረጋቸውን ገልጧል። 


1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now

አውስትራሊያ ለገቡ የዩክሬን ስደተኞች ለሶስት ዓመታት የሥራ፣ የትምህርትና የሜዲኬይር ግልጋሎቶች ተጠቃሚ የሚያደርግ ቪዛ ተፈቀደ | SBS Amharic