ኮሮናቫይረስ በሁለት ዓመታት ውስጥ ያበቃል - የዓለም ጤና ድርጅት

*** ኮቪድ - 19 ቪክቶሪያ ውስጥ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ከ200 በታች ወርዷል

Amharic News 22 August, 2020

World Health Organisation Director-General Tedros Adhanom Ghebreyesus. Source: Courtesy of KEYSTONE

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም - የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከ1918ቱ ወረርሽን ባነሰና ከሁለት ዓመታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እንደሚያበቃ አስታወቁ።

ምንም እንኳ ወረርሽኙ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ተስፋፍቶ ያለና አውሮፓ ውስጥ አገርሽቶ ቢገኝም የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ ከ1918ቱ ወረርሽኝ ጋር በማነጻጸር ወረርሽኙ በሁለት ዓመት ሊያከትም እንደሚችል ሲያመላክቱ፤ 

"ሉላዊነት፣ ቅርርቦሽና ትስስሮሽ አሉታዊ ጎን ቢሆኑብንም፤ በአዎንታዊ ጎኑ የተሻለ ቴክኖሎጂ ስላለን ከሁለት ዓመታት ባነሰ ጊዜ ወረርሽኙ ለመክላት ተስፋ አናደርጋለን" ብለዋል።

አክለውም፤ ፈጥኖ ክትባት የማግኘቱ ተስፋ እንደ 1918ቱ ወረርሽኝ ዘለግ ያለ ጊዜ እንደማይወስድ ገልጠዋል። 

በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም ከ 22.8 ሚሊየን በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ሲሆን 793,382 ሕይወታቸውን አጥተዋል።

  ቫይረስ - ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ ውስጥ የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ቁጥር እየቀነሰ ነው።

በዛሬው ዕለት 182 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 13 ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል። 

የቪክቶሪያ ዋና የጤና ኃላፊ ፕሮፌሰር ብሬት ሳተን እያሽቆለቆለ የመጣው የቫይረሱ ተላላፊነት ቁጥር አበረታች እንደሆነ ሲገልጡ፤

"ለሁለት ቀናት በተከታታይ ከ200 በታች ወርዶ ማየቱ መልካም ነው። እርግጥ ነው፤ ማሽቆልቆሉ እየቀጠለ ነው። ሆስፒታላችንም ውስጥ እንዲሁ መረጋጋት እያሳየ ነው። ሆስፒታል ተኝተው የሚታከሙ ሰዎች፣ የፅኑ ሕሙማን ክፍል ታካሚዎችና ሌላው ቀርቶ የመተንፈሻ መሳሪያ ተጠቃሚ ህሙማን ቁጥር እንኳ እየቀነሰ ነው። እናም አዎንታዊ በሆነ መልኩ ቀጥሏል። በዚሁ ሁኔታ ከዘለቅን፤ በሚቀጥለው ሳምንት የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር በቀን ከ150 በታች ወርዶ እንመለከታለን" ብለዋል። 

በሌላም በኩል ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓታት ከ31 ሺ  የኮሮናቫይረስ ምርመራ ዘጠኝ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

ቫይረስ - ኩዊንስላንድ 

ደቡብ - ምሥራቅ ኩዊንስላንድ ውስጥ አዲስ የቤት ውስጥና ከቤት ውጪ ገደቦች ተጣሉ።

በዛሬው ዕለት ዘጠኝ ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን ስድስቱ ከብሪስበን የወጣቶች ማቆያ ማዕከል ጋር የተያያዙ ናቸው።

በብሪስበንና አካባቢዋ በቤት ውስጥና ከቤት ውስጥ ውጪ ከ10 በላይ ሰዎች እንዳይሰባሰቡ ተወስኗል።  

ይህም Brisbane, Logan, Scenic Rim, the Lockyer Valley, Somerset, Moreton, Redlands እና Ipswich ያካትታል።

 

 

 


Share

2 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service