የምያንማር የተቃውሞ ሰልፈኞችን ሞት ተከትሎ ተጨማሪ ማዕቀብ ለመጣል እየታሰበ ነው

*** ሎሬየት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን አረፉ

Amharic News 21 February 2021

Source: SBS Amharic

የአውሮፓ ሕብረትና እንግሊዝ አንግ ሳን ሱ ቺን በመፈንቅለ መንግሥት አስወግዶ ስልጣን የጨበጠውን የምያንማር ወታደራዊ መንግሥት በመቃወም የሁለት ሕይወቶች ማለፍን ተከትሎ ተጨማሪ ማዕቀብ ለመጣል እያሰቡ ነው።

የተቃውሞው መጠን እየበረታ የመጣ ሲሆን፤ የሰሞኑን የማንዳላይ ተቃውሞ ሰልፍ ለመበተን ፖሊስ እውነተኛ ጥይቶችን መተኮሱን የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል። 

እስካሁን ዩናይድ ስቴትስ፣ እንግሊዝ፣ ካናዳና ኒውዝላንድ ወታደራዊ መሪዎቹ ላይ ያነጣጠሩ ማዕቀቦችን ጥለዋል።

ባለፈው ሳምንት ምያንማር መዲና ናይፒይዳው ጭንቅላቷ ላይ በጥይት ተመትታ ለሞት የበቃችውን የ20 ዓመት ወጣት የተቃውሞ ሰልፈኛ ምያ ትዊት ትዊት ካይንን አክሎ የሟቾች ቁጥር ሶስት ደርሷል።

Amharic News 21 February 2021
Protesters take to the streets of Yangon to protest against the military coup and demanded the release of Aung San Suu Kyi on 19 February. Source: Getty

ጥበበ የማነ ብርሃን

ሎሬየት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን የካቲት 13 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም ዜና ዕረፍቱን አስመክተው የተሰማቸውን ኃዘን ሲገልጡ "በሕክምና ሞያ፣ በሀገር ሽማግሌነት፣ በርዳታ አስተባባሪነት እና በዕርቀ ሰላም ኮሚሽን አባልነት ሀገራቸውን ያገለገሉት የዓለም ሎሬት ዶር ጥበበ የማነ ብርሃን ማረፋቸውን በመስማቴ የተሰማኝን ኃዘን እገልጣለሁ። ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸውና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ መጽናናትን እመኛለሁ" ብለዋል።

Laureate Dr Tibebe Yemane Berhan.
Laureate Dr Tibebe Yemane Berhan. Source: FBC

ዶ/ር ጥበበ በሙያቸው ዘርፍ በዓለም አቀፍ የምርምር ማዕከላትና የማሰልጠኛ መካነ ተቋማት በተመራማሪ ስይንቲስቲነትና የሕዝብ ጤና ሥራ አስኪያጅነት ከአንድ አሠርት ዓመት በላይ አገልግለዋል። ከ65 በላይ ሳይንሳዊ ጥናቶቻቸውም በዓለም የጥራት ደረጃቸው የላቀ ጆርናሎች ላይ ለሕትመት በቅተዋል።

ዶ/ር ጥበበ ሐሩራዊ በሽታዎችን በ2020 በቁጥጥር ስር አውሎ መክላት እንዲቻል ግፊት ሲያደርጉ ነበር።   

ሱዳንና ግብፅም ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ልዩነቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን አበርክተዋል።

በሙያቸው ዘርፍ ላበረከቷቸው ዓለም አቀፍ አስተዋፅዖዎቻቸውም ከአሜሪካ ግለታሪካዊ መካነ ተቋም ያገኙትን የዓለም ሎሬየት አክሎ በርካታ የክብር ሽልማቶችን ያገኙ ሲሆን ከራሺያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲንም የፑሽኪን ሜዳል ተሸልመዋል።

ዶ/ር ጥበበ በሕይወት ሳሉ ጎልፍ መጫወት፣ ረቂቅ ሙዚቃ ማድመጥና መጽሐፍትን ማንበብ ይወዱ ነበር። ከባለቤታቸው ዶ/ር ያለም አምባየም ሁለት ሴት ልጆችን አፍርተዋል። ሁለት የልጅ ልጆችም አሏቸው።

 

ቴኒስ አውስትራሊያ 

በሴቶች ዓለም አቀፍ የሜዳ ቴኒስ አሸብራቂ ኮከብ እየሆነችው የመጣችው ናኦሚ ኦሳካ የዘንድሮው የአውስትራሊያ ኦፕን 2021 ቴኒስ አሸናፊ ሆናለች።

ናኦሚ ትናንት ፌብሪዋሪ 20 ሜልበርን በተካሔደው የመጨረሻ የአውስትራሊያ ኦፕን ለአሸናፊት የበቃችው አሜሪካዊቷን ጄኔፈር ብራዲን 6-4 6-3 በመርታት ነው።

Naomi Osaka
Japan's Naomi Osaka holds the Daphne Akhurst Memorial Cup at the Australian Open tennis championship in Melbourne, Australia, Saturday, Feb. 20, 2021. Source: AAP

ገና የ23 ዓመት ወጣትና የአራት ግራንድ ስላም አሸናፊ የሆነችው ናኦሚ ከዊሊያምስ እህትማማቾችና ኪም ክላስተር በስተቀር በርካታ ግጥሚያዎች በማሸነፍ ከሌሎች ሴት ቴኒስ ተጫዋቾች የላቁ ድሎችን በማህደሯ አስፍራለች።

 

 

 

 


2 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now