የፌዴራል ተቃዋሚ ቡድን ምክር ቤት አባላት በኢንዶኔዥያ ላይ ድንበር በመዝጋትና አለመዝጋት ጉዳይ ተለያይተዋል

'Hasta la vista, baby!' የቦሪስ ጆንሰን የፓርላማ ስንብት ቃል

News

Opposition M-Ps Karen Andrews (L), David Littleproud (C) and, Barnaby Joyce (R). Source: Getty

የፌዴራል ተቃዋሚ ቡድን የግብርና ቃል አቀባይ በእግርና አፍ በሽታ ሳቢያ አውስትራሊያ በኢንዶኔዥያ ላይ ድንበሯን እንድፀጋ እንደማይፈልጉ ሲያስታውቁ ሌሎች የተቃዋሚ ቡድኑ ምክር አባላት የአውስትራሊያ ድንበር እንዲዘጋ የሚሹ መሆኑን እየገለጡ ነው። 

የድንበር መዘጋቱን እሳቤ እየገፉ ያሉት የተቃዋሚ ቡድን አባላት የሊብራል ፓርቲዋ ካረን አንድሩስ እና የናሽናልስ ፓርቲ ባርናቢ ጆይስ ናቸው።

ከግል የምክር ቤት አባላት ውስጥም ሴናተር ጃኪ ላምቢ አውስትራሊያ በጊዜያዊነት በኢንዶኔዥያ ላይ በሯን እንድዘጋ የሚሹ መሆኑን ገልጠዋል።

ሆኖም የተቃዋሚ ቡድኑ የግብርና ቃል አቀባይና ምክትል መሪ ዴቪድ ሊትልፕራውድ በኢንዶኔዥያ ላይ ድንበርን መዝጋት የተቃዋሚ ቡድኑ ይፋ አቋም አይደለም ሲሉ አስታውቀዋል። 

በሌላ በኩል የግብርና ሚኒስትር ማሪ ዋት ባሊ የነበሩ በተለይም የቁም ከብቶችና እርሻ አካባቢ የነበሩ መንገደኞች የእግርና አፍ በሽታን ወደ አውስትራሊያ ይዘው እንዳይገቡ ጫማቸውንና ልብሶቻቸውን በውል እንዲያፀዱ፤ በተለይም ሊጠቀሙበት የማይሿቸው ጫማዎች ካሏቸው እዚያው ጥለዋቸው እንዲመጡ ምክረ ሃሳብ ሰጥተዋል።

ቦሪስ ጆንሰን

ተሰናባቹ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ረቡዕ ዕለት ለእንግሊዝ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር "Hasta la vista, baby!" በ "ደህና ሁኑ" የስንብት ቃል ተሰናብተዋል።
News
Prime Minister Boris Johnson speaks during Prime Minister's Questions in the House of Commons, London. Source: Getty
በስልጣን ላይ በነበሩት ወቅት ካደረጓቸው ሁነኛ ተግባራት ካሏቸው ውስጥ እንግሊዝን ከአውሮፓ ኅብረት ማስወጣት መቻላቸውን፣ የኮቪድ 19 ክትባትን ለስኬት ማብቃታቸውንና ለዩክሬይን ያደረጓቸውን ድጋፎች ነቅሰው አንስተዋል።

ጆንሰንን ለመተካት የቀድሞው የፋይናንስ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እና የቀድሞዋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ ማጣሪያዎችን አልፈው በዕጩነት ቀርበዋል።
News
Conservative leadership candidate Rishi Sunak (L) and Liz Truss (R). Source: Getty


 

 


Share

Published

Updated

By NACA, Kassahun Seboqa

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service