የተወሰኑ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪዎች ከብርቱ ጎርፎች ለማምለጥ ቀዬአቸውን ለቅቀው ሊወጡ ነው

*** በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ዓለም አቀፍ ተመልካቾች በቶኪዮ ኦሎምፒክ እንዳይታደሙ ተወሰነ

SBS Amharic

Source: SBS Amharic

ኒው ሳውዝ ዌይልስ ወንዞቿ ሞልተው በመፍሰሳቸው ግድቦቿን ለመጥለቅለቅ፣ መንገዶቿን ለመዘጋትና አያሌ ነዋሪዎችም በመጪዎቹ ሰዓታት ቀዬአቸውን ለቅቀው ለመውጣት በቋፍ እንዲገኙ ግድ ብሏል።

ፕሪሚየር ግላዲስ በርጂክሊያን የመካከለኛ ሰሜን ባሕር ዳርቻ ሃንተር፣ ሴንትራል ኮስት፣ ሜትሮፖሊታን ሲድኒና ዋራጋምባ ግድብ አካባቢ ነዋሪዎች መኖሪያዎቻቸውን ለቅቀው ለመውጣት ስንዱ እንዲሆኑ አሳስበዋል።

Floods
Strike Team Zulu help residents of a residential village in Port Macquarie evacuate safely on Saturday, 20 March, 2021. Source: Fire and Rescue NSW

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ስቴት ድንገተኛ አደጋ ግልጋሎት ከማርች 18 ጀምሮ ከ4,000 በላይ የእርዳታ ስልክ ጥሪዎችን ተቀብሏል።

የድንገተኛ አደጋ ግልጋሎት ሚኒስትር ዴቪድ ኤልየት ሰዎች ጎርፎች መካከል በተሽከርካሪዎች ለማለፍ ወይም በእግር ለማቋረጥ እንዳይጥሩ አሳስበዋል። 

ቶኪዮ ኦሎምፒክ

በዘንድሮው የቶኪዮ ኦሎምፒክና ፓራሊምፒክስ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ የባሕር ማዶ ተመልካቾች እንዳይታደሙ በአዘጋጆች ተወስኗል።

የዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚደንት ቶማስ ባኽና የዓለም አቀፍ ፓራሊምፒክስ ኮሚቴ ዋና ኃላፊ አንድሩ ፓርሰንስ ለውድድሩ ተሳታፊዎችና ለጃፓን ሕዝብ ደህንነት ሲባል የቶኪዮን ውሳኔ እንደሚቀበሉ መግለጣቸውን የቶኪዮ ኦሎምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ ፕሬዚደንት ሴይኮ ሃሺሞቶ ገልጠዋል።

የቶኪዮ ኦሎምፒክ መካሄድ የነበረበት ባለፈው ዓመት ቢሆንም በወረርሽኙ የተነሳ ዘንድሮ ጁላይ 23 የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ይካሄዳል።

የኦሎምፒክ ችቦ ቅብብሎሽ ጥብቅ የሆነ ሥነ ንጽሕና ፕሮቶኮልን ተከትሎ በማርች 25 ይጀምራል።

የቶኪዮ ኦሎምፒክ ውድድሮችን በሥፍራው ተገኝተው ለመመልከት በባሕር ማዶኞች የተቆረጡ 630,000 ቲኬቶች ገንዘብ ለባለቤቶቹ የሚመለስ መሆኑን የኮሚቴው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቶሺሮ ሙቶ አስታውቀዋል።


1 min read

Published

By NACA



Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now