የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚደንት ሙዋይ ኪባኪ በ90 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የወቅቱ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ገለጡ።
ፕሬዚደት ኬንያታ ለቀድሞው ፕሬዚደንት ሕልፈተ ሕይወት አስባብ ምን እንደሆነ አላስታወቁም።
ሆኖም ፕሬዚደንቱ በጠና ታምመው የነበረ መሆኑ በኬንያ ጋዜጠኞች ዘንድ ሲነገር ቆይቷል።
በምጣኔ ሃብት ከእንግሊዝ ዩኒቨርሲቲ የተመረቁት ኪባኪ ሶስተኛው የኬንያ ፕሬዚደንት ሲሆኑ ከ2003-2013 በስልጣን ላይ ቆይተዋል።
በስልጣን ላይ ሳሉ ትምህርትን ጨምሮ የተለያዩ የማሻሻያ የለውጥ እርምጃዎችን የወሰዱ ቢሆንም ሙሰኝነትን መከላከል አቅቷቸዋል በሚል ሲወቀሱ ነበር።
በዲሴምበር 2007ቱ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ከ 1,200 በላይ ኬንያውያን ሕይወቶች ማለፉም በፕሬዚደንታዊ ውርሰ አሻራቸው ላይ በአሉታዊ ገፅታ ተነሺ ሆኗል።
ፕሬዚደንታዊ ስልጣናቸውን ሲለቁ የተተኩት በምክትል ፕሬዚደንታቸው ዳንኤል አራፕ ሞይ ነበር።
የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት
የኢትዮጵያ የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤቱ ዛሬ ሚያዚያ 14 - 2014 ባወጣው የደኅነነትና ፀጥታ መግለጫ ተገቢ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ግድ መሰኘቱን አስታወቀ።
ምክር ቤቱ የእርምጃ ትኩረት አቅጣጫዎቹን ሲያመላክት፤
- ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ቡድኖችንና ግለሰቦችን፣ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማሠራጨት ሕዝብና ሀገርን ሰላም የሚነሡ አካላትን፣ በሕገ ወጥ መንገድ ታጥቀው የሕዝብን ሰላም የሚነሡና ለታሪካዊ ጠላቶቻችን በተላላኪነት የሚያገለግሉ ቡድኖችን፣ በመሬት ወረራና በተለያዩ የሥርቆትና የማታለል ተግባራት የተሠማሩትን፣ የትራንስፖርትና ሕዝብ እንቅስቃሴዎችን የሚያውኩትን፣ የልማትና የኢንቨስትመንት ተግባራትን የሚያደናቅፉ እና
- በተመሳሳይ የምግብና ልዩ ልዩ ሸቀጦች ዋጋ እንዲንር በሕገ ወጥ መንገድ ምርት የሚያከማቹ፣ በኮንትሮባንድ መልክ ነዳጅና ሌሎች ምርቶችን ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚያሾልኩ ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ተገቢው እርምጃ ይወሰዳል ሲል ገልጧል።

