በዋና ሚኒስትር ማይክል ገነር የሚመራው የኖርዘን ቴሪቶሪ ሌበር መንግሥት ትናንት ማምሻውን ሰፊ ባልሆነ ድምፅ ዳግም አናሳ ወይም አብላጫ ወንበሮች ያሉት መንግሥት ለማቆም የሚያስችለውን ድምፅ ለማግኘት ተቃርቧል።
የኖርዘን ቴሪቶሪ ፓርላማ ካለው 25 የፓርላማ ወንበር ውስጥ አብላጫ ወንበሮችን አሸንፎ መንግሥት ለመመሥረት የሚያሻው 13 ወንበሮችን ማግኘት ሲሆን፤ ሌበር 11 የተረጋገጡ ወንበሮችን አሸንፏል።
የካንትሪ ሊብራል ፓርቲ 3 ወንበሮችን ሲያገኝ ሌሎች 2 ወንበሮችን ወስደዋል፤ 7 የምክር ቤት ወንበር ድምፆች ተቆጥረው ስላላለቁ አሸናፊዎቻቸው ገና አልተወሰነም።
ሆኖም፤ የሌበር መሪ ማይክል ገነር ዋና ሚኒስትር ሆነው እንደሚመለሱ ያላቸውን እምነት ሲገልጡ "ሌበር የኖርዘርን ቴሪቶሪን መንግሥት እንደሚያቆም ከፍ ያለ እምነት አለኝ" ብለዋል።
ትናንት ማምሻውን ተቆጥረው ያልተጠናቀቁ የድምፅ ካርድ ቆጠራዎች ዛሬ ማለዳ 10:00am ላይ መቆጠር ቀጥለዋል።
የምርጫ ድምጾቹ እየተቆጠሩ የሚገኙባቸው የምክር ቤት ወንበሮች Arnhem, Araluen, Barkly, Brennan, Braitling, Daly እና Namatjira ናቸው።
ሌበር 60 ፐርሰንት ያህል ተቆጥረው ካሉባቸውና ተጨማሪ ወንበሮችን ሊያሸንፍ ይችልባቸዋል ከተባሉት aly, Fong Lim, Barkly, Arnhem ወይም Namatjira ውስጥ ሁለት ወንበሮችን ካሸነፈ አብላጫ ወንበሮች ያሉት መንግሥት መመሥረት ይችላል።
ብልፅግና ፓርቲ - ደቡብ ክልል
የደቡብ ሕዝብ ብሔራዊ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ከነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ በዎላይታ ዞን የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ከፓርቲዉና ከመንግስት ሥራ ኃላፊነታቸዉ እንዲነሱ የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴ መወሰኑን አስታወቀ።
የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴ ይህን ያስታወቀው በዎላይታ ዞን ወቅታዊ የፀጥታና የፖለቲካ ሁኔታን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው።
ከዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ግድ የተሰኘውም "በክልል የመደራጀት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ በብልፅግና ፓርቲ እና በመንግስት ከፍተኛ ርብርብ በሚደረግበት በአሁኑ ወቅት ዎላይታ ዞንን እንዲመሩ ኃላፊነት የወሰዱ አመራሮች ከፓርቲዉ ዲስፒሊንና ከተሰጣቸዉ ህዝባዊና መንግስታዊ ኃላፊነት በተቃራኒ በመቆም የህዝቡን ጥያቄ ሽፋን በማድረግ ለዉጡን ለማደናቀፍ በግልፅና በህቡዕ ተደራጅቶ ከሚንቀሳቀሱ የዉስጥ እና የዉጪ ኃይሎች ጋር እየሰሩ እንዳሉ" በመረጋገጡ እንደሆነ ገልጧል።

